
ባሕር ዳር: ግንቦት 11/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ስማርት ስልኮች ለሥራ ግንኙነት፣ ለኦንላይን ግብይት፣ ለባንክ አገልግሎት፣ ለሶሻል ሚዲያ እና መሰል የዕለት ተዕለት ተግባራት ጥቅም በመስጠት ላይ ይገኛሉ።
በዚህም ምክንያት ስልኮች የሰዎችን አድራሻ፣ የካርድ መረጃዎችን እና የባንክ አካውንት ምስጢራዊ ቁጥሮችን ጨምሮ በርካታ የግል መረጃዎችን ይይዛሉ።
ይህ የኢንተርኔት አጠቃቀም ደግሞ ስልኮችን በቫይረስ እንዲጠቁ በር ይከፍታል። ቫይረሶች የስልኮችን አፈጻጸም ከመቀነስ ባለፈ፣ ሃከሮች የገንዘብ ጥቅም ለማግኘት መረጃዎችን እንዲሠርቁ ያደርጋሉ።
🚫የምንጠቀምበት ስልክ በቫይረስ እንዴት ሊጠቃ ይችላል?
👉በኢሜይል ወይም በአጭር የጽሑፍ መልዕክት የሚላኩ ያልተረጋገጡ ሊንኮችን (Links) ወይም ፋይሎችን መክፈት
👉ማራኪ መስለው የሚታዩ ነገር ግን የኋላ ኋላ ማልዌር የሚያወርዱ አደገኛ ማስታወቂያዎችን መንካት
👉የስልኩን የደኅንነት ማስጠንቀቂያዎች ችላ በማለት አጠራጣሪ ድረ ገጾችን መጎብኘት
👉መተግበሪያዎችን ከታመኑት “አፕ ስቶር” እና “ጎግል ፕሌይ ስቶር” ውጭ ካሉ ይፋዊ ካልኾኑ ድረ-ገጾች ማውረድ”
👉ጥበቃ በሌላቸው እና ክፍት በኾኑ የሕዝብ ነፃ ዋይፋይ (Public Wi-Fi) አውታረ መረቦች ላይ መገናኘት
#ስልክ በቫይረስ መጠቃቱን እንዴት ማወቅ ይቻላል፦
👉 ያልተለመዱ ማስታዎቂያዎች እና አዳዲስ አፖች ይታያሉ
👉የስልክ ሙቀት ከመጠን በላይ መጨመር
👉የስልክ ፍጥነት ባልተለመደ ኹኔታ መቀነስ
👉የኢንተርኔት ዳታ (Data) በከፍተኛ ኹኔታ መባከን
👉የባትሪ ኃይል በፍጥነት መድረቅ ወይንም ማለቅ ይከሰታል።
🚫ስልክ በቫይረስ እንዳይጠቃ ምን ይደረግ?
👉መተግበሪያዎችን ከታመኑ መደብሮች (App Store ወይም Google Play Store) ብቻ ማውረድ እና ከማውረድ በፊት የተጠቃሚዎችን አስተያየት (Reviews) ማንበብ።
👉ለእያንዳንዱ የኢንተርኔት አካውንት ጠንካራ እና የተለያዬ የይለፍ ቃል (Password) መጠቀም።
👉በአጭር መልዕክት ወይም በኢሜይል የሚላኩ አጠራጣሪ ሊንኮችን አለመንካት።
👉በኢንተርኔት የተጎበኙ ድረ ገጾች ዝርዝር እና በስልኩ ውስጥ የተከማቹ አላስፈላጊ ጊዜያዊ ፋይሎችን በየጊዜው ማጥፋት።
👉በብሮውዘር ላይ የይለፍ ቃል (Login Information) አለማስቀመጥ እና ከተጠቀሙ በኋላ ሁልጊዜ መውጣት (Log out ማድረግ)።
👉የስልኩን የአሠራር ሥርዓት (OS) እና መተግበሪያዎች በየጊዜው ማዘመን (Update ማድረግ)።
👉ደኅንነታቸው ያልተጠበቁ እንደ ሕዝብ ነፃ ዋይፋይ ያሉ የኢንተርኔት መስመሮችን አለመጠቀም ይገባል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
