ሥልጣን የሚገኘው በካርድ ብቻ ነው።

5
ባሕር ዳር: ግንቦት 11/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የመራዊ ከተማን ወደ ቀደመ አስተማማኝ ሰላሟ ለመመለስ ከሚደረገው ጥረት ጎን ለጎን ሰባተኛውን ጠቅላላ ምርጫ በተሳካ ሁኔታ ለማጠናቀቅ ከፍተኛ ዝግጅት እየተደረገ መኾኑን የመራዊ ከተማ አሥተዳደር አስታውቋል።
የመራዊ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ ብርሃኑ አበራ ነዋሪዎች የሥልጣን ሽግግር ከሰላማዊ መንገድ ውጭ ሊሳካ እንደማይችል በመገንዘብ በከፍተኛ ንቅናቄ የምርጫ ካርድ ማውጣታቸውን ገልጸዋል።
ሕዝቡ ሥልጣን የሚገኘው በኃይል ሳይኾን በሰላማዊ መንገድ እና በካርድ ብቻ ነው ብሎ ያምናል፤ በዓደባባይ በሚደረጉ የምርጫ ቅስቀሳዎች ላይ የሚታየው ተሳትፎም የዚሁ ማሳያ ነው ብለዋል። ይህም ማኅበረሰቡ በነጻነት የራሱን መሪ ለመምረጥ ያለውን ጽኑ ፍላጎት ያሳየ እንደኾነ ተናግረዋል። ምርጫውን በስኬት ለማጠናቀቅም የተለያዩ ቅድመ-ዝግጅቶች እየተደረጉ መኾናቸውን አንስተዋል።
ማኅበረሰቡ ከሥነ-ልቦና፣ ከኢኮኖሚ እና ከማኅበራዊ ጫናዎች መውጣት የሚችለው በምርጫ ብቻ መኾኑን አስገንዝበዋል።
ሕዝቡ ሰላምን፣ መረጋጋትን እና የኢኮኖሚ እድገትን በሚያረጋግጥ መልኩ ነጻ፣ ገለልተኛ እና ፍትሐዊ በኾነ የምርጫ ሂደት ላይ በመሳተፍ የራሱን ዕድል በራሱ እንዲወስንም ጥሪ አቅርበዋል።
ዘጋቢ፦ ስማቸው አጥናፍ
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !
Previous articleየምርጫ ቅስቀሳ የሕዝብን ደኅንነት ያስቀደመ የሀሳብ መድረክ ይሁን!
Next article“ጀግንነትን ተላብሰን የአማራን ሕዝብ ከማንኛውም ጥቃት እየጠበቅን ነው ” የአድማ መከላከል ሠራዊት