
ባሕር ዳር: ግንቦት 10/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) “የመረጃ ሉዓላዊነት ለፖሊሲ ነጻነት” በሚል መሪ መልዕክት በተዘጋጀው ሀገራዊ ጉባኤ ላይ ተገኝተዋል።
በጉባኤው ላይ መልዕክት ያስተላለፉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) መረጃ ልክ እንደ ወርቅ ውድ የሀገር ሀብት ነው ብለዋል።
ጠንካራ ሀገረ መንግሥት ለመገንባት፣ የመረጃ እና የፖሊሲ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ ቁልፍ ጉዳይ መኾኑን ገልጸዋል።
ከሌሎች በሚገኝ መረጃ ላይ ሙሉ ለሙሉ መደገፍ የፖሊሲ ነጻነትን የሚያሳጣና ትክክለኛነቱ የሚያጠራጥር ነው ብለዋል። የራስን መረጃ በሀገር ልጅ መሰብሰብ እና መተንተን ትልቅ ሀገራዊ ኩራትና ዋስትና መኾኑን ገልጸዋል።
ለዚህም የዳታ ምንጮችን በማብዛትና እርስ በርስ በማነፃፀር የጠራና የዘመነ የመረጃ ሥርዓት መዘርጋት ለሀገር እድገት ወሳኝ ሚና ይጫወታል ነው ያሉት።
ጥራት እና ተደራሽነትን በላቀ ደረጃ ለማረጋገጥ ደግሞ በአሁኑ ወቅት የሰው ሠራሽ አስተውህሎት (AI) ቴክኖሎጂን በግል እና በመንግሥት ተቋማት ውስጥ በጥልቀት መጠቀም አስፈላጊ እንደኾነ አመላክተዋል።
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
