‎”የመረጃ ትኩረታችን በዜጎች ሕይወት በሚታዩ ተጨባጭ ለውጦች ላይ መሆን አለበት።” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)

2
ባሕር ዳር: ግንቦት 10/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በማህበራዊ ገጻቸው ባጋሩት መልእክት ”የመረጃ ሉዓላዊነት ለፖሊሲ ነጻነት” በተሰኘውና ኢትዮጵያ በመረጃና በስታቲስቲክስ የሉዓላዊነት ጉዞ ያስመዘገበችውን ትልቅ ድል በተበሰረበት ሀገራዊ ጉባኤና ኤግዚቢሽን ላይ ተገኝቼ የተመለከትኩት የዘርፉ እመርታ እጅግ አስደሳች ሆኖ አግኝቼዋለሁ ብለዋል።
‎መረጃ የዚህ ዘመን ስትራቴጂካዊ ሀብት እና ጠንካራ ሀገረ መንግሥት የሚገነባበት ቁልፍ የሉዓላዊነት ምሰሶ ነው። የተዋሰ አሊያም በውጭ አካላት ላይ ጥገኛ የሆነ መረጃ ሀገራዊ መሻታችንን ማሳካት ስለማያስችል፤ የፖሊሲ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ የራስን መረጃ በራስ አቅም መሰብሰብ እና መተንተን ወሳኝ ግብዓት መኾኑን አመላክተዋል።
‎ከሁሉም በላይ፤ የመረጃ አሰባሰብና ትንተና ሥራ በሀገር ልጆች እውቀትና ክህሎት ሲከወን ማየት ታላቅ ሀገራዊ ኩራት ነው። ከዚህ በተጨማሪ የመረጃ ትኩረታችን በቁጥር በሚገለጹ ውጤቶች ላይ ብቻ ሳይሆን ሰው ተኮር በሆኑና በዜጎች ሕይወት በሚታዩ ተጨባጭ ለውጦችም ላይ መሆን አለበት ነው ያሉት።
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !
Previous article“የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር የተፈጥሮን ጉዳት እያከመ ለመኾኑ የሀሮማያ ሐይቅ ህያው ማሳያ ነው” ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመሥገን ጥሩነህ