“የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር የተፈጥሮን ጉዳት እያከመ ለመኾኑ የሀሮማያ ሐይቅ ህያው ማሳያ ነው” ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመሥገን ጥሩነህ

3
ባሕር ዳር፡ ግንቦት 10/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በምሥራቅ ሐረርጌ በነበራቸው ጉብኝት የሀሮማያ ሐይቅን ተመልክተዋል። ባስተላለፉት መልእክትም “የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር የተፈጥሮን ጉዳት እያከመ ለመኾኑ የሀሮማያ ሐይቅ ህያው ማሳያ ነው” ብለዋል።
የሀሮማያ ሐይቅ ዳግም መወለድ አረንጓዴ አሻራ ከሰጠን ፍሬዎች አንዱ ስለመኾኑም ገልጸዋል። በ1996 ዓ.ም ሙሉ በሙሉ ጠፍቶ የነበረው የሀሮማያ ሐይቅ፣ በአረንጓዴ አሻራ እና በተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ጥረት ዛሬ ወደ ቀደመ ውበትና ሥሪቱ መመለሱን አንስተዋል። ይህም አረንጓዴ አሻራን ለኢትዮጵያ የውኃ አካላትና ለተፋሰስ ልማት ቁልፍ ኢኒሼቲቭነቱን በተግባር ያረጋገጠ ነው።
ይህ ስኬት በመደመር እሳቤ ልማትን ማረጋገጥ ብቻ ሳይሆን፣ የተፈጥሮን ጫና መቋቋም እና መግራት እንደሚቻል ማረጋገጫ ነው ብለዋል ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።
በቦታው ሲደርሱ አቀባበል ላደረገላቸው ሕዝብም ምስጋና አቅርበዋል።
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous article”የበደልነውን ሕዝባችንን ለመካስ የሰላም አማራጭን ተከትለናል” ሰላምን የተቀበሉ ታጣቂዎች
Next article‎”የመረጃ ትኩረታችን በዜጎች ሕይወት በሚታዩ ተጨባጭ ለውጦች ላይ መሆን አለበት።” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)