“ብልጽግና የገባውን ቃል የፈጸመ፣ የልማት ሥራዎችን ያስፋፋ፣ የሕዝቦችን ተጠቃሚነት ያረጋገጠ ፓርቲ ነው ” አብዱ ሁሴን (ዶ.ር)

5
ባሕር ዳር: ግንቦት 10/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች በሐይቅ ከተማ የምርጫ ቅስቀሳ አካሂደዋል።
የሐይቅ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ ከድር ሙሐመ
ከተማዋ ለዘመናት ተዘንግታ መኖሯን አስታውሰው ከለውጡ ማግስት የልማት ተጠቃሚ መኾኗን ተናግረዋል።
መንግሥት በአካባቢው የሎጎ ሐይቅን በማልማቱ ወጣቶች የሥራ ዕድል ተጠቃሚ እንዲኾኑ አስችሏል ነው ያሉት።
የንጹሕ መጠጥ ውኃ አቅርቦት፣ የትምህርት ቤት ግንባታ፣ ሐይቅን ከአጎራባች ክልል ጋር የሚያገናኝ የሐይቅ ጭፍራ መንገድ ግንባታ እና የተለያዩ ልማቶች መንግሥት የማኅበረሰቡን የዘመናት ጥያቄ እየመለሰ መኾኑን ማሳያ ናቸው ብለዋል።
የኮሪደር ልማቱ የኅብረተሰብ ተሳትፎ የተረጋገጠበት እና በ130 ሚሊዮን ብር የተገነባ መኾኑን ተናግረዋል።
የደቡብ ወሎ ዞን አሥተዳዳሪ አሊ መኮንን ብልጽግና ኋላቀርነትን እና ድህነትን ለማጥፋት በትኩረት እየሠራ ነው ብለዋል። በዞኑ የተለያዩ የልማት ሥራዎች እየተተገበሩ መኾኑን ገልጸዋል።
የዞኑ ሕዝብ በመስኖ፣ በአትክልት እና ፍራፍሬ፣ በሌማት ትሩፋት ውጤታማ ተግባር እንዲከናወን እየተሠራ ነው ብለዋል።
በዞኑ 110 መሠረተ ልማቶች በቅርቡ ለምርቃት እንደሚበቁም አንስተዋል። የሕዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ብልጽግናን ምረጡ ብለዋል።
የአማራ ክልል ምክትል ርእሰ መሥተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ.ር) የሐይቅ ከተማን ከጉስቁልና በማንሳት ብልጽግና የተለያዩ የልማት ተጠቃሚ እንድትኾን አድርጓል ብለዋል።
የኮሪደር ልማቱ የከተማዋን ውበት የገለጠ መኾኑን አንስተዋል። ልማት በአንድ አካባቢ እንዲረጋገጥ ከተፈለገ ሕዝብ በታሪኩ ከፍታ ልክ ቆሞ መተባበር እና መደገፍ ያስፈልጋል ብለዋል።
ወሎ የሥነ መንግሥትን ታሪክ የሚያውቅ እና የሚያከብር ነው ያሉት ምክትል ርእሰ መሥተዳድሩ ሰላሙን እንዲያጸና አሳስበዋል።
ብልጽግና የገባውን ቃል የፈጸመ፣ የልማት ሥራዎችን ያስፋፋ፣ የሕዝቦችን ተጠቃሚነት ያረጋገጠ በመኾኑ ግንቦት 24/2018 ዓ.ም ብልጽግናን ምረጡ ብለዋል።
መጭው ጊዜ ለአማራ ሕዝብ ትንሳኤ ነውም ብለዋል። ከተሞች እንዲዋቡ የንግድ እንቅስቃሴያቸው እንዲሳለጥ፣ መሠረተ ልማታቸው እንዲስፋፋ ብልጽግና ይሠራልም ነው ያሉት።
በቀጣዩ አምስት ዓመት ኢትዮጵያ የባሕር በር ባለቤትነቷን የምታረጋግጥበት፣ ከፍታዋን የምታጸናበት እና የከተሞቿ የልማት ተጠቃሚነት የሚረጋገጥበት በመኾኑ ብልጽግናን ምረጡ ነው ያሉት።
ዘጋቢ:- ያየህ ፈንቴ
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleብሔራዊ የአቮካዶ ልማት ፕሮግራም ተቀርጾ ወደ ሥራ መግባቱን የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ አስታወቀ።
Next articleበአማራ ክልል ለ860 ሺህ ተጋላጭ ወገኖች የሚውል የ1 ነጥብ 15 ቢሊዮን ብር ፕሮጀክት ይፋ ተደረገ!