🇪🇹”ብልጽግና ፓርቲ አፍሪካዊ ተምሳሌት የኾነች ሀገር የመገንባት ራዕይ ይዞ እየሠራ ነው” ምክትል ከንቲባ አስሜ ብርሌ

2

 

ባሕር ዳር፡ ግንቦት 09/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ለከተማዋ የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጭ ባለንብረቶች የምርጫ ቅስቀሳ አካሂዷል። 🚐🚕

የከተማ አሥተዳደሩ ምክትል ከንቲባ አስሜ ብርሌ በዚህ ወቅት እንደገለጹት መርሐ ግብሩ የፓርቲውን የምርጫ ምልክት እና እጩ ተወዳዳሪዎችን ለማስተዋወቅ ያለመ ስለመኾኑም አብራርተዋል።

የብልጽግና ፓርቲ መደመርን እሳቤ አድርጎ የሚጓዝ፣ ሁለንተናዊ ብልጽግናን መዳረሻው አድርጎ የሚሠራ ፓርቲ ነው ብለዋል። ኅብረ ብሔራዊ አንድነት ያላት ሀገር ለመገንባት ራዕይ ይዞ የሚጓዝ ፓርቲ ስለመኾኑም አስረድተዋል።

በኢትዮጵያ ሰብዓዊ ልዕልናን በማረጋገጥ፣ ኢኮኖሚያዊ ሉዓላዊነትን በማሳካት አፍሪካዊ ተምሳሌት የኾነች ሀገር ለመገንባት እየሠራ መኾኑንም አስረድተዋል።

ብልጽግና ፓርቲ ለባሕር ዳር ከተማ ልማት ልዩ ትኩረት በመስጠት በአፍሪካ በተምሳሌትነት የምትጠቀስ ተመራጭ ከተማ እንድትኾን ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ መኾኑንም አንስተዋል።

ለዚህም በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የባሕር ዳር ከተማን የከፍታ ጉዞ እውን የሚያደርጉ እጩዎች ቀርበዋል ነው ያሉት።

መራጮች በካርድ ማውጣት በስፋት እንደተሳተፉ ሁሉ በምርጫው ዕለትም በነቂስ ወጥተው እንዲመርጡ እና በንቃት እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርበዋል።🗳️🚶‍♂️🚶‍♀️✅

ዘጋቢ:- አሰፋ ልጥገበው

#አሚኮ #ምርጫ_2018 #ኢትዮጵያ

የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ

https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

Previous articleየአማራ ክልል ከፍተኛ መሪዎች የአዋሽ፣ ኮምቦልቻ፣ ሃራ ገበያን የባቡር ፕሮጀክት ዳግም ሥራ አስጀመሩ።
Next article🚆”የአዋሽ – ኮምቦልቻ – ሀራ ገቢያ የባቡር ፕሮጄክት ወደ ሼል መግባት መንግሥት የሕዝብን ጥቅም ለማረጋገጥ እንደሚሠራ ያሳየ ነው” አብዱ ሁሴን (ዶ.ር)