የአማራ ክልል ከፍተኛ መሪዎች የአዋሽ፣ ኮምቦልቻ፣ ሃራ ገበያን የባቡር ፕሮጀክት ዳግም ሥራ አስጀመሩ።

2

 

ባሕር ዳር: 09/2018 ዓ.ም (አሚኮ) 392 ኪሎ ሜትር የሚሸፍነው የባቡር መንገድ ፕሮጀክቱ 2007 ዓ.ም ተጀምሮ እስከ 2012 ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቅ ነበር። ኾኖም በሰሜኑ ጦርነት በደረሰበት ውድመት እና ዘረፋ ምክንያት ለመገባደድ ተቃርቦ የነበረው ፕሮጀክት ተስተጓጉሎ ቆይቷል።

ይህ ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ያለው ፕሮጀክት መጠናቀቅ የንግድ ሥርዓቱን በማሳለጥ፣ የሥራ ዕድል በመፍጠር ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋል። የባቡር መስመሩ በኤሌክትሪክ ኀይል የሚሠራ ነው።

የአማራ ክልል ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬ፣ የአማራ ክልል ምክትል ርእሰ መሥተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ.ር) ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል።

ዘጋቢ:- ያየህ ፈንቴ

የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ

https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !

Previous article“የከተማ ነዋሪዎችን የኑሮ ዘይቤ ለመቀየር እና የምርት ባሕልን ለማሳደግ የሌማት ትሩፋት ትልቅ አስተዋጽዖ አለው” ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመሥገን ጥሩነህ
Next article🇪🇹”ብልጽግና ፓርቲ አፍሪካዊ ተምሳሌት የኾነች ሀገር የመገንባት ራዕይ ይዞ እየሠራ ነው” ምክትል ከንቲባ አስሜ ብርሌ