“የከተማ ነዋሪዎችን የኑሮ ዘይቤ ለመቀየር እና የምርት ባሕልን ለማሳደግ የሌማት ትሩፋት ትልቅ አስተዋጽዖ አለው” ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመሥገን ጥሩነህ

2

 

ባሕር ዳር፡ ግንቦት 09/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሐረር ከተማ እየተከናወኑ ያሉትን የማር፣ የወተትና የዶሮ እርባታ የሌማት ትሩፋት ሥራዎችን ተዘዋውረን ጎብኝተዋል።

በከተማው በኢኒሼቲቩ በግለሰብና በመንግሥት ደረጃ ሼዶችን በመገንባት የማር፣ የወተት፣ የእንቁላልና የአሳ መንደሮችን የማቋቋም ሥራ በስፋት እየተሠራ ይገኛል ብለዋል

እንደ ሀገር የአመጋገብ ሥርዓታችንን ከመሰረቱ ለመቀየር እና በምግብ እራስን ለመቻል ትልቅ ትርጉም የሚሰጠው ይህ ተግባር ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል። የእንሳት፣ የዶሮና ዓሳ ዝርያ ማሻሻልና መኖ ማቀነባበሪያዎች ላይም ትኩረት ተሰጥቶት እየተሠራበት ይገኛል ሲሉ ተናግረዋል።

#አሚኮ #visit #ኢትዮጵያ

የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ

https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !

Previous articleየፓኪስታን የሀገር ውስጥ ሚኒስትር ሞህሲን ናቂቭ ቀውሱን ለማርገብ ቴህራን ገብተዋል።
Next articleየአማራ ክልል ከፍተኛ መሪዎች የአዋሽ፣ ኮምቦልቻ፣ ሃራ ገበያን የባቡር ፕሮጀክት ዳግም ሥራ አስጀመሩ።