
ባሕር ዳር: ግንቦት 09/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የጉብኝታቸው ዓላማ በኢራን እና አሜሪካ መካከል የተቋረጠውን የሰላም ንግግር ማስቀጠል ነው። እንዲሁም ከሆርሙዝ የባሕር መስመር መዘጋት ጋር የተያያዘውን ቀውስ ማርገብ ይፈልጋሉ።
የኢራን አይአርኤንኤ (IRNA) እና መህር (Mehr) የዜና ወኪሎች ጉብኝቱን ዘግበውታል። ፓኪስታን በሁለቱ ወገኖች መካከል እንደ አስታራቂ እየሠራች ነው።
የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ታሂር አንደራቢ የሰላም ሂደቱ መቀጠሉን ባለፈው ወር ገልጸው ነበር።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራቅቺ በኒው ዴልሂ መግለጫ ሰጥተዋል። ከአሜሪካ ጋር ለሚደረገው ድርድር ትልቁ እንቅፋት አለመታመን መኾኑን ገልጸዋል። ኾኖም ከቀጣናው ሀገራት ለሚቀርብ ዲፕሎማሲያዊ ድጋፍ ዝግጁ መኾናቸውን ጠቁመዋል።
በአሁኑ ወቅት በተዋዋዮቹ መካከል የተኩስ አቁም ስምምነት አለ። ኾኖም ኢራን በሆርሙዝ ወሽመጥ ላይ የጣለችውን ገደብ አላነሳችም። አሜሪካም በኢራን ወደቦች ላይ የምታደርገውን እገዳ ቀጥላለች። ይህ ሁኔታ በዓለም አቀፍ የነዳጅ ገበያ ላይ አለመረጋጋት ፈጥሯል።
በስማቸው አጥናፍ
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ
https://linktr.ee/Amharamediacorporations
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !
