📢 የጣና በለስ ስኳር ፋብሪካ 5 ሺህ ሠራተኞችን ይፈልጋል።

8

 

ባሕር ዳር: ግንቦት 09/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የጣና በለስ ስኳር ፋብሪካ ወደ ማምረት ገብቷል። ፋብሪካው በርካታ ማሽነሪዎች የሚንቀሳቀሱበት እና ሰፊ የእርሻ ኢንቨስትመንት የሚከናወንበት ዘርፈ ብዙ ጥቅም የሚሰጥ ነው።

ከፋብሪካው የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው በሙሉ አቅሙ ወደ ሥራ ሲገባ ከ24 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ያለማል። በቀን ከ12 ሺህ ኩንታል በላይ ስኳርም ያመርታል።

🚜 ለዚህ ሁሉ የሥራ እንቅስቃሴም ከ23 ሺህ በላይ ዜጎችን በቋሚ እና በጊዜያዊነት በመቅጠር ሰፊ የሥራ ዕድል የመፍጠር አቅም ያለው ግዙፍ ፕሮጀክት ነው።

የጣና በለስ ስኳር ፋብሪካ ዋና ሥራ አሥኪያጅ ባይነሳኝ ዘሪሁን ለአሚኮ እንደተናገሩት በአሁኑ ወቅት ፋብሪካው ዳግም ወደ ምርት መሸጋገሩን ተከትሎ የሠራተኛ እጥረት አጋጥሟል ብለዋል።

ፋብሪካው በቀጣይ ውጤታማ ሥራ ለማከናወን በፊት ከነበረው ሠራተኛ በተጨማሪ አዲስ 5 ሺህ ሠራተኞችን እንደሚፈልግ አስታውቀዋል።

በቀጣይም የማምረት አቅሙን እያሳደገ ስለሚሄድ ከዚህ በላይ የሥራ ዕድል በመፍጠር ለአካባቢው ማኅበረሰብ እና ለሥራ ፈላጊ ወገኖች መልካም ዕድልን ይዞ የመጣ ስለመኾኑም አመላክተዋል።

በየደረጃው ያለው የሚመለከተው የመንግሥት አመራር እና መዋቅርም የፋብሪካውን የሠራተኛ እጥረት ለሥራ ዕድል መፍጠሪያ አማራጭ እንዲጠቀሙበት እና የሰው ኃይል በማቅረብ እንዲተባበር መልዕክት አስተላልፈዋል።

ይህንን በመገንዘብ ሥራ ፈላጊ ወጣቶች ወደ ፋብሪካው መጥተው የሥራ ዕድሉ ተጠቃሚ እንዲኾኑም ጥሪ አቅርበዋል።

ዘጋቢ:- አሰፋ ልጥገበው

#አሚኮ #ጣና_በለስ #ስኳር_ፋብሪካ #ኢትዮጵያ🇪🇹

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ስፖርት የተሻለ ትውልድ ለመፍጠር ቁልፍ ጉዳይ በመኾኑ ብልጽግና ፓርቲ ለዘርፉ መጠናከር በልዩ ትኩረት እየሠራ ነው” ዋና አፈ ጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬ