“የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ እና የተፋሰስ ልማት ወደተሻለ የልማት ከፍታ እየተሸጋገረ ነው” ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመሥገን ጥሩነህ

2

 

ባሕር ዳር፡ ግንቦት 08/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ሐረርጌ በግራዋ ወረዳ የልማት ሥራዎችን ጎብኝተዋል። ጉብኝታቸውን አስመልክቶ የሚከተለውን መልእክት አስተላልፈዋል፦

ታሪክን እና ውብ መልክዓ ተፈጥሮን የታደለው ጋራሙለታ የኢትዮጵያን ሜዳና ተራሮች ምርት የሚታፈስባቸው የማድረግ ጉዟችን ማሳያ ሆኗል።

አካባቢው በግብርና ልማት እንዲሁም በተቀናጀ የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃና የተፋሰስ ልማት ይበልጥ ወደተሻለ የልማት ከፍታ እየተሸጋገረ ነው።

ዛሬ በኦሮሚያ ክልል በምስራቅ ሃረርጌ በግራዋ ወረዳ ሜይራ ጉዲና ቀበሌ የተመለከትነው የተፋሰስ ልማት ለአካባቢ ጥበቃ ብቻ ሳይሆን ለምርትና ምርታማነት ማደግ ወሳኝ ሚና አለው።

በተቀናጀ መልኩ እየለሙ የሚገኙ የፍራፍሬ፣ የደን ልማት እና አጠቃላይ የግብርና ሥራዎች ለሀገራዊ የግብርና ሽግግር ተደማሪ አቅምን የሚፈጥሩ ናቸው።

የወረዳው አርሶ አደሮች በክላስተር በመደራጀት በአትክልት እና ፍራፍሬ፣ በእንስሳት ሃብት ልማት እና በንብ ማነብ የተቀናጀ ግብርና እያከናወኑት ያለው ሥራ የሚበረታታ ነው፤ የምግብ ሉዓላዊነትን የማረጋገጥ ሀገራዊ ንቅናቄን ለማሳካትም አጋዥ ሚና ይኖረዋል።

በአካባቢው ስንደርስ ለተደረገልን አቀባበል እና ለተቸረን ሕዝባዊ አክብሮት ልባዊ ምስጋና ለማቅረብ እወዳለሁ።

የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ

https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !

Previous articleጎንደር ዩኒቨርሲቲ የሕክምና ተማሪዎቹን አስመረቀ።
Next articleርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ የዓባይ ሲሚንቶ ፋብሪካን ጎበኙ።