
ደብረ ታቦር፡ ግንቦት 08/2018ዐዓ.ም (አሚኮ) በደቡብ ጎንደር ዞን የፋርጣ ወረዳ የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት አካል ጉዳተኞችን ያሳተፈ ለሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ የምረጡኝ ቅስቀሳ መድረክ አካሂዷል።
የደቡብ ጎንደር ዞን አሥተዳደር ማዕድን መምሪያ ኀላፊ ብርቄ ፀጋ በመድረኩ ላይ እንደገለጹት፤ የሰባተኛውን ጠቅላላ ምርጫ ልዩ የሚያደርገው አረጋውያንን፣ ሴቶችን እና አካል ጉዳተኞችን ልዩ ትኩረት ሰጥቶ ማሳተፉ ነው።
በመኾኑም አካል ጉዳተኞች ሕገ-መንግሥታዊ መብታቸውን ተጠቅመው እንዲመርጡ ጠይቀዋል።
የፋርጣ ወረዳ ዋና አሥተዳዳሪ ይርጋ ጌትነት ፤ ብልጽግና ፓርቲ በቃል ብቻ ሳይኾን በተግባር የሚሠራ፣ የሴቶችን እና የአካል ጉዳተኞችን ተሳትፎ በተጨባጭ እያረጋገጠ የሚገኝ ፓርቲ በመኾኑ፣ አካል ጉዳተኞች የመምረጥ መብታቸውን ተጠቅመው ብልጽግናን እንዲመርጡ ጥሪ አቅርበዋል።
የወረዳው ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ አማረ ይሁኔ፤ ሰባተኛው ሀገራዊ ምርጫ ፍጹም ሰላማዊ ኾኖ እንዲጠናቀቅ የአካል ጉዳተኞች ተሳትፎ አይተኬ መኾኑን ጠቅሰው፣ ፓርቲያቸው የአካል ጉዳተኞችን መብት እና ጥቅም በማስከበር ረገድ ግንባር ቀደም መኾኑን አብራርተዋል።
በምረጡኝ ቅስቀሳ መርሐ-ግብሩ ላይ የተሳተፉ አካል ጉዳተኞች ለአሚኮ በሰጡት አስተያየት፤ መብታቸውን የሚያስከብርላቸውን እና ከሁሉም ማኅበረሰብ ጋር እኩል ተሳታፊ የሚያደርጋቸውን ፓርቲ ለመምረጥ መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል።
የምርጫ ካርዳቸውን አውጥተው ድምጽ ለመስጠት እየተጠባበቁ መኾኑን እና በምርጫው መሳተፋቸው ደስተኛ እንዳደረጋቸው የገለጹት አስተያየት ሰጭዎቹ፤ ምርጫው ፍጹም ሰላማዊ ኾኖ እንዲጠናቀቅ ሁሉም አካል ኀላፊነቱን መወጣት እንዳለበት አሳስበዋል።
#አሚኮ #ዜና #7ኛው_ምርጫ #ፋርጣ_አማራክልል #ኢትዮጵያ🇪🇹
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ
https://linktr.ee/Amharamediacorporations
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !
