
ሰቆጣ: ግንቦት 08/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የሰቆጣ ከተማ አሥተዳደር ብልጽግና ፓርቲ የምረጡኝ ቅስቀሳ በሰቆጣ ከተማ በተሽከርካሪዎች የታገዘ የድጋፍ ሰልፍ አካሂዷል።
በቅስቀሳው የተሳተፉ የብልጽግና ፓርቲ ደጋፊዎች የአካባቢያችንን ሰላም ጠብቀን የሀገርን ብልጽግና እናስቀጥላለን ብለዋል።
ወይዘሮ አሰፉ ታደለ እና አቶ አማኑኤል አዳነ ፓርቲውን በመደገፍ በቅስቀሳው ተገኝተዋል። እንደ ሀገር እየታዩ ያሉ የልማት ለውጦች አበረታች እንደኾኑ ተረድተናል ብለዋል።
በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አሥተዳደር መንግሥት በርካታ የልማት ፕሮጀክቶችን እየሠራ መኾኑንም ጠቁመዋል።
የአካባቢያችንን ሰላም እየጠበቅን ሰባተኛውን ጠቅላላ ምርጫ በስኬት ለማካሄድ የበኩላችን ሚና እንወጣለን ነው ያሉት።
የሰቆጣ ከተማ አሥተዳደር ብልጽግና ፓርቲ የፖለቲካ ዘርፍ ኀላፊ መላሽ ደሳለኝ ፤ ኢትዮጵያን ወደ ነበረ ከፍታዋ ለመመለስ ብልጽግና ፓርቲ በትኩረት እየሠራ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
የሰቆጣ ከተማ ሕዝብ በተሽከርካሪ ታግዞ ያደረገው የድጋፍ ሰልፍ ለብልጽግና ትልቅ የአደራ እና የቃል ኪዳን ሰነድ ነው ብለዋል። ምርጫው ተጀምሮ እስኪጠናቀቅ የአካባቢውን ሰላም ለማጽናት ከምንጊዜውም በላይ መሥራት እንደሚገባም አንስተዋል።
በምረጡኝ ቅስቀሳው የሰቆጣ ምርጫ ክልል የብልጽግና ፓርቲ እጩዎች ከሕዝብ ጋር የተዋወቁ ሲኾን ቅስቀሳውም በሰላም ተጠናቅቋል።
ዘጋቢ፦ ደጀን ታምሩ
🕊️🗳️ #ድጋፍ #ምርጫ2018 #ኢትዮጵያ🇪🇹
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ
https://linktr.ee/Amharamediacorporations
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !
