
ደብረ ማርቆስ: ግንቦት 08/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከዓመታት በኋላ የመጀመሪያ የሙከራ በረራውን ወደ ደብረ ማርቆስ አድርጓል።
ከዓመታት በኋላ ወደ ደብረ ማርቆስ በረራ ያደረገችው አውሮፕላን የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ፣ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል፣ ምክትል ርእሰ መሥተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ.ር) እና ሌሎችን ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች ይዛ ደብረ ማርቆስ ደርሳለች።
እንግዶቹ ደብረ ማርቆስ ሲደርሱ ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል። የደብረ ማርቆስ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ በመጠናቀቅ ላይ ነው። የአውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ ለዓመታት የሕዝብ ጥያቄ ነበር። ግንባታው የሕዝብ ጥያቄን የመለሰ ነው።
ዘጋቢ:- ታርቆ ክንዴ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/Amharamediacorporations
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
