ምርጫ የሥልጡንነት መገለጫ!

4
ባሕር ዳር፡ ግንቦት 07/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ብልጽግና ፓርቲ “ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር” በሚል መሪ ሀሳብ ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ምልክት ትውውቅ እና የምረጡኝ ቅስቀሳውን በዳንግላ ከተማ አካሂዷል።
በመድረኩ ላይ የተገኙት የአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ምክትል አስተዳዳሪ አይተነው ታዴ ብልጽግና ተጨባጭ ሀገራዊ ልማቶችን ሠርቶ ያሳየ እና እየሰራም ያለ ፓርቲ ስለመኾኑ ገልጸዋል።
የከተሞችን ውበት ይበልጥ በመግለጥ ለነዋሪዎች ምቹ ለማድረግም ኮሪደር ልማት ላይ በስፋት እየሠራ ይገኛል ብለዋል። የግብርና ምርት እና ምርታማነትን በማሳደገ ረገድ ውጤቶችን ማስመዝገቡን ገልጸዋል።
ብሔረሰብ አሥተዳደሩ በርካታ የብልጽግና ቱሩፋቶች ተጠቃሚ መሆኑን ያነሱት አቶ አይተነው በቅርቡ ወደ ሥራ የተመለሰውን የጣና በለስ ስኳር ፋብሪካ እንዲሁም ስድስት የሚሆኑ የአስፋልት መንገዶች በቀጣይ የሚጠናቀቁ መሆናቸውንም ተናግረዋል።
“ምርጫ የሥልጡንነት መገለጫ ነው” ያሉት ምክትል አሥተዳዳሪው ሕዝቡ በቀጣይ አምስት ዓመታት የሚመራውን መሪ ለመምረጥ መብቱን እንዲጠቀም አስገንዝበዋል።
የዳንግላ ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ካሳሁን አስማረ ብልጽግና በሁሉም ዘርፎች ለውጥ እያመጣ ያለ ፓርቲ ነው ብለዋል።
ትልልቅ ፕሮጀክቶችን ጀምሮ የሚፈጽም ፓርቲ እንደሆነም ተናግረዋል ።
የመድረኩ ተሳታፊዎችም ብልጽግና ሁለንተናዊ ለውጥ ውስጥ ያለ በመሆኑ ቀጣይም ከፓርቲው ጎን ኾነው እንደሚሠሩ ገልጸጸዋል።
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleየንጹሕ ውኃ አቅርቦትን እና የአርሶ አደሮችን ተጠቃሚነት ያረጋገጠው የማንጎ ልማት።
Next article“የምክክር ባሕል እንደ ኢትዮጵያ ላሉ ሀገራት እጅግ አስፈላጊ ነው” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)