
ባሕር ዳር፡ ሰኔ 08/2018 ዓ.ም(አሚኮ) አንጋፋው የባሕል ሙዚቃ ድምጻዊ ሰማኸኝ በለው (ሰሜ ባላገሩ) ባደረበት ሕመም በሕክምና ሲረዳ ቆይቶ በዛሬው ዕለት ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱ ተሰምቷል።
ድምጻዊ ሰማኸኝ በለው በተለይም የሀገራችንን ባሕላዊ እሴቶች የጠበቁ፣ ማኅበራዊ ሕይወትንና ገጠራማውን የአኗኗር ዘይቤ የሚያንጸባርቁ በርካታ ተወዳጅ የሙዚቃ ሥራዎችን ለአድማጭና ተመልካች በስፋት ማበርከቱ ይታወቃል።
የአራቱ ልጆች አባትና ባለትዳር የነበረው የድምጻዊ ሰማኸኝ በለው ባደረበት ሕመም በሕክምና ሲረዳ ቆይቶ በዛሬው ዕለት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል፡፡
አሚኮ በታዋቂው ድምጻዊ ሰማኸኝ በለው ሕልፈት የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን እየገለጸ፥ ለቤተሰቦቹ፣ ለወዳጅ ዘመዶቹ እንዲሁም ለአድናቂዎቹ በሙሉ መጽናናትን ይመኛል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/Amharamediacorporations
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
