
ጎንደር :ግንቦት 07/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ከጎንደር ከተማ የተለያዩ ክፍለ ከተሞች የተውጣጡ ወጣቶች ለብልጽግና ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳ እና የድጋፍ ሰልፍ አካሂደዋል።
“በላቀ የወጣቶች ተሳትፎ ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር” የማሸጋገር ራዕይ በሚል መሪ መልዕክት የተካሄደው የወጣቶች የድጋፍ ሰልፍ ወጣቶች የሀገርን አንድነት እና የልማት ቱርፋቶች ለማስቀጠል የድርሻቸውን እንደሚወጡ የሚያሳይ ነው ተብሏል።
ወጣቶቹ ሰላማዊ እና ዴሞክራሲያዊ ምርጫ እንዲካሄድ የበኩላቸውን እንደሚወጡ ተናግረዋል። ለፓርቲው ያላቸውን ድጋፍ በተለያዩ መልዕክቶች ገልጸዋል።
በጎዳና ሰልፉ የተገኙት የጎንደር ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ቻላቸው ዳኘው ብልጽግና ፓርቲ ለወጣቶች ተጠቃሚነት እና ለከተማዋ የኮሪደር ልማት የሰጠው ትኩረት ከፍተኛ መኾኑን አስታውቀዋል።
ብልጽግና ፓርቲ ችግሮችን እየፈታ፣ እንቅፋቶችን እየተሻገረ ወደ ፊት መራመድን ባሕል አድርጎ እየሠራ መኾኑን ጠቁመዋል። ወጣቶች የተጀመሩ የልማት እና የሰላም እንቅስቃሴዎች ውጤታማ እንዲኾኑ የሚያደርጉትን ጥረት አጠናክረው እንዲቀጥሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ዘጋቢ፦አዲስ ዓለማየሁ
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !
