
ባሕር ዳር፡ ግንቦት 07/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በደብረ ማርቆስ ከተማ አሥተዳደር 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ አስመልክቶ የምርጫ ቅስቀሳ እና ውይይት እየተካሄደ ነው።
መድረኩ ላይ በምክትል ርዕሰ መሥተዳደር ማዕረግ የገጠር ዘርፍ አስተባባሪ ድረስ ሳህሉ (ዶ.ር)፣ የአማራ ክልል ሚሊሻ ኮምሽን ኮሚሽነር አስቻለ አላምሬ እንዲሁም የክልል እና የከተማ አሥተዳደሩ የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል። የደብረ ማርቆስ ከተማ የሀገር ሽማግሌዎች እና የሃይማኖት አባቶች የውይይቱ ተሳታፊ ኾነዋል።
ምርጫው ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊ፣ ታማኝ እና ፍትሐዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የበኩላቸውን እንደሚወጡ ተሳታፊዎቹ አረጋግጠዋል።
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
