ተመካክሮ፣ ተወያይቶ እና ተግባብቶ ሀገርን ማሻገር ያስፈልጋል።

4
ባሕርዳር፡ ግንቦት 07/2018ዓ.ም (አሚኮ) የባሕርዳር ከተማ አሥተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊ ኾኖ እንዲጠናቀቅ ከሃይማኖት አባቶች እና ከሀገር ሽማግሌዎች ጋር እየመከረ ነው።
የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጎሹ እንዳላማው ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ በሰላም እንዲካሄድ እየተሠራ መኾኑን ገልጸዋል። ከሃይማኖት አባቶች እና ከሀገር ሽማግሌዎች ጋር መመካከር አስፈላጊ መኾኑንም ተናግረዋል።
ብዙ ሀገራት ከምርጫ በኋላ ወደ ግጭት እና አላስፈላጊ ነገር ይገባሉ፤ ይህም ለብዙ ጉዳት ዳርጓቸዋል፤ እኛ ደግሞ ይህ እንዳይኾን ቀድመን እንሠራለን ነው ያሉት።
በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ የሃይማኖት ተቋማት እና የሃይማኖት አባቶች በሀገረ መንግሥት ግንባታ እና በሰላም ላይ ከፍ ያለ ሚና እንዳላቸውም ጠቅሰዋል። አሁንም የሰላም አስተምሯቸው ላቅ ያለ እንዲኾን ጠይቀዋል።
የሃይማኖት አባቶች ስለ ሀገር፣ ስለ ሰላም፣ ስለ አንድነት እና ስለፍቅር ስለሚጸልዩ እና ስለሚያስተምሩ ይህ ጸንቶ እና ዕውን ኾኖ ማየት እንደሚፈልጉ ገልጸዋል።
ምርጫው ትልቅ ሀገራዊ ፋይዳ ያለው ነው ያሉት ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባው የዘንድሮው ጠቅላላ ምርጫ ከዚህ በፊት ከነበሩት የምርጫ ጊዜያት በተለየ መልኩ የሚታይ እንደኾነም አንስተዋል።
በቀጣይ ጊዜ ተመካክረን፣ ተወያይተን እና ተግባብተን ሀገርን ማሻገር ያስፈልጋል ነው ያሉት።
ዘጋቢ፦ ሮዛ የሻነህ
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !
Previous articleየሀገር ሰላም አምባሳደሮች ኾነን ምርጫውን ማስኬድ አለብን።
Next articleምርጫ ለዴሞክራሲዊ ሀገር!