“ብልጽግናን መምረጥ የነገዋን ዘመናዊት ኢትዮጵያ እና የወጣቶችን ብሩህ ተስፋ ማረጋገጥ ነው” የጎንደር ከተማ የድጋፍ ሰልፈኞች

3
ባሕር ዳር፡ ግንቦት 07/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የጎንደር ከተማ ወጣቶች 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ አስመልክተው ለብልጽግና ፓርቲ ያላቸውን ድጋፍ በሕዝባዊ ሰልፍ እየገለጹ ነው።
የኢትዮጵያን ክብር ከፍ ለማድረግ፣ የባሕር በር አማራጮችን ለማስፋት እና ሁለንተናዊ ብልጽግናን እውን ለማድረግ የተጀመረው ጉዞ በጠንካራ መሠረት ላይ እንደሚገኝ ወጣቶቹ በሰልፉ ላይ እያነሱ ነው።
ብልጽግናን መምረጥ ማለት ፍትሕ የሰፈነባት፣ ዴሞክራሲ የጸናባት እና የዜጎች ኩራት የታደሰባትን ሀገር የመገንባት ታሪካዊ ዕድልን መጠቀም ማለት ነውም ብለዋል። ባለፉት የለውጥ ዓመታት የታዩት ስኬቶች የነገዋን ታላቅ ኢትዮጵያ ለመገንባት መነሻዎቻችን ናቸው ነው ያሉት ወጣቶቹ።
የዜጎችን የኑሮ ጥራት የሚያሻሽሉ የኮሪደር ልማቶች፣ የዘመናዊ ትምህርትና ጤና ተቋማት ግንባታ እንዲሁም የዲጂታል ኢኮኖሚ ትልሞቻችን በላቀ ፍጥነት እናስቀጥላለን ብለዋል። ሰውተኮር የልማት ተግባራት ለከተሞቻችን አዲስ ገጽታ፣ ለዜጎች ደግሞ ምቹ የኑሮ አካባቢን እየፈጠሩ እንደሚገኙም አንስተዋል። “ብልጽግናን መምረጥ የነገዋን ዘመናዊት ኢትዮጵያ እና የወጣቶችን ብሩህ ተስፋ ማረጋገጥ ነው” ሲሉም በአደባባይ መልእክታቸው አስተጋብተዋል።
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleየፕላስቲክ ክልከላው ተራዘመ?
Next articleሰላማዊ የምርጫ ሥርዓት ለዴሞክራሲ መሠረት ነው።