
በአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የዴሞክራሲ ባሕል ግንባታ ዘርፍ ኀላፊ መስፍን አበጀ (ዶ.ር) በምርጫው ለመሳተፍ የሚያስችል ሰፊ የፖለቲካ ምሕዳር መኖሩን ተናግረዋል።
በዚህም ከበፊቱ በተሻለ መንገድ ፓርቲዎች ፕሮግራሞቻቸውን እና አማራጭ ሀሳቦቻቸውን በተለያዩ አማራጮች ሲያስተዋውቁ መቆየታቸውንና እያስተዋወቁ መሆኑን አብራርተዋል።
የሚያጋጥሙ ችግሮችንም በየጊዜው እየተገናኙ በመፍታት ለምርጫው ዝግጅት ለማድረግ አስቻይ ሁኔታዎች እንደተፈጠሩም ነው የተናገሩት።
በሂደቱም በክልሉ የፖለቲካ ምሕዳሩ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ መምጣቱን የሚያመላክት ስለመኾኑም ተናግረዋል።
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
