
ባሕር ዳር፡ ግንቦት 06/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከቻይናው አቻቸው ጋር በወቅታዊ ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ መክረዋል።
ፕሬዚዳንት ትራምፕ በቤጂንግ ቆይታቸው የመካከለኛው ምሥራቅ ጦርነት ዘላቂ መፍትሄ በሚያገኝበት ሁኔታ እና የሁለቱን ሀገራት የሁለትዮሽ ግንኙነት ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ሰፊ ምክክር አድርገዋል።
አልጀዚራን ጨምሮ የተለያዩ ዓለም አቀፍ የዜና አውታሮች እንደዘገቡት ሁለቱ ሀገራት ኢራን በፍፁም የኒውክሌር ጦር መሣሪያ ባለቤት መኾን የለባትም በሚለው ቁልፍ ጉዳይ ላይ የጋራ ስምምነት ላይ ደርሰዋል።
በተጨማሪም የአሜሪካ እና የቻይና መንግሥታት ለዓለም አቀፍ ንግድ እና ለነዳጅ ዝውውር ወሳኝ የኾነው የሆርሙዝ የባሕር መስመር ለማንኛውም እንቅስቃሴ ክፍት ኾኖ መቆየት እንዳለበት አቋማቸውን ማጠናከራቸውን የዋይት ሃውስ ባለስልጣንን ዋቢ አድርጎ አልጀዚራ ዘግቧል።
ይህ የመሪዎቹ ስምምነት በመካከለኛው ምሥራቅ ያለውን ውጥረት ለማርገብ እና ለዓለም አቀፍ ኢኮኖሚ መረጋጋት ትልቅ ፋይዳ ይኖረዋል ተብሎ ይጠበቃል።
በስማቸው አጥናፍ
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ
https://linktr.ee/Amharamediacorporations
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
