
ባሕር ዳር፡ ግንቦት 06/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የዓለማችን የሁለቱ ኀያላን ሀገራት ቻይና እና አሜሪካ መሪዎች ትላንት ግንቦት 05/2018 ዓ.ም በቤጅንግ ተገናኝተዋል። ዛሬም በቤጂንግ የተካሄደው የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና የፕሬዝዳንት ሺ ጂንፒንግ ጉባኤ በአሜሪካ እና በቻይና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ውስጥ ትልቅ ምዕራፍ የተመዘገበበት ኾኗል።
ሁለቱ መሪዎች በታላቁ የቻይና የሕዝብ አዳራሽ ካደረጉት ወሳኝ ሥብሠባ በኋላ፣ የቻይና የታሪክ እና የባሕል ምልክት የኾነውን የ15ኛው ክፍለ ዘመን ሥሪት “የሰማይ ቤተ መቅደስ” መጎብኘታቸውን ፎክስ ኒውስ ዘግቧል።
በአሚናዳብ አራጋው
#አሚኮ #ዲትዮጵያ #America #china #visit
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ
https://linktr.ee/Amharamediacorporations
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
