
ባሕር ዳር፡ ግንቦት 06/2018ዓ.ም (አሚኮ) የአንዲት ሀገር የዴሞክራሲ ጉዞ ስኬት የሚለካው የምርጫ ሂደት በጠንካራ የሕግ ማዕቀፍ ሲጠበቅ እና ሕዝብ በነፃነት ድምጹን መስጠት ሲችል ነው።
ምርጫ የዜጎች የሥልጣን ባለቤትነት መገለጫ ነው። ይህ መብት ያለ አግባብ እንዳይቀለበስ የራሱ የኾኑ የሕግ ድንጋጌዎች አሉት። ብዙዎቻችን መምረጥ እና መመረጥን እንደ መብት ብቻ እናየዋለን፤ ነገር ግን በዚህ ሂደት ውስጥ የሚፈጸሙ ጥፋቶች ከእስራት እስከ መብት መታገድ የሚያደርሱ ከባድ ቅጣቶችን እንደሚያስከትሉ ያውቃሉ?
ይህ መሠረታዊ መርሕ በኢፌዲሪ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 9(3) ላይ በግልጽ ተደንግጓል ይላሉ።
ምርጫው ሰላማዊ እና ፍትሐዊ እንዲኾን ከቅድመ ምርጫ እስከ ድምጽ ቆጠራ ድረስ ሊከበሩ የሚገባቸው የሕግ ማዕቀፎች መኖራቸውን ጠቁመዋል።
ሕጉ ማንኛውም ዜጋ፣ ዕጩ ተመራጭ ወይም የፖለቲካ ፓርቲ እንዳይፈጽማቸው በጥብቅ የከለከላቸው ነጥቦች የሚከተሉት ናቸው።
ለምርጫ ተብሎ ሥብሠባ በማድረግ ሂደቱን መረበሽ ወይም ዜጎች እንዳይመርጡ እና እንዳይመረጡ እንቅፋት መኾን።
ዕድሜያቸው ያልደረሰ ሕፃናት እንዲመዘገቡ ወይም እንዲመርጡ ማግባባት እና መገፋፋት።
የምርጫ ውጤትን ለማዛባት የእጅ መንሻ (ጉቦ) መስጠት ወይም መቀበል።
የምርጫ ሳጥን እና ኮሮጆዎችን መስረቅ ወይም ማጥፋት፣ የድምጽ መስጫ ወረቀቶችን ማበላሸት እና የምርጫ ፖስተሮችን ኾን ብሎ መቅደድ። የምርጫ ቅስቀሳ ማድረግ ከተከለከለ በኋላ ማንኛውንም ዓይነት የቅስቀሳ ሥራ ማከናወን።
ለምዝገባ የሚቀርቡ አባላትን ቁጥር ማጭበርበር፣ ሀሰተኛ የሀብት እና የዕዳ መግለጫ ማቅረብ፣ በመንግሥት እና በሕዝብ የተመደበን የምርጫ በጀት ለሌላ ዓላማ ማዋል፣ በምርጫ ወቅት የጦር መሣሪያ ይዞ መንቀሳቀስ በፓርቲዎች ምዝገባ አዋጅ (1162/2011) በጥብቅ የተከለከሉ ናቸው።
ምርጫ የነገ ዕጣ ፈንታችንን የምንወስንበት ታላቅ መድረክ ነው። ይህ መድረክ በሕገ-ወጥነት እንዳይበላሽ ደግሞ በሕገ መንግሥቱ የተደነገጉ የምርጫ ሕጎችን እና አዋጆችን ማክበር እና ተገዥ መኾን ግድ ይላል። ሕግን ማክበር መብትን ማክበር ነውና።
ዘጋቢ ፦ ቴዎድሮስ ደሴ
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !
