የባንክ ሂሳብዎን ከብሔራዊ መታወቂያ ጋር አስተሳስረዋል?

2
🚫
ባሕር ዳር: ግንቦት6/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የሁሉም ባንክ ደንበኞች እስከ ግንቦት 6 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ሂሳባቸውን ከፋይዳ ቁጥር (ብሔራዊ መታወቂያ) ጋር ማስተሳሰር እና ማጠናቀቅ እንዳለባቸው ብሔራዊ ባንክ ማሳሰቡ ይታወሳል።
እስከ ዛሬ ግንቦት 6/2018 ዓ.ም የባንክ ሂሳብን ከብሔራዊ መታወቂያ ጋር ማስተሳሰር ግድ የሚላቸው👇
-ባሕር ዳር
-ጎንደር
-ደሴ
-ደብረ ብርሃን
-ኮምቦልቻ
-አዲስ አበባ
-ሀረሪ
-ድሬዳዋ አስተዳደር
-ሀዋሳ
-አርባ ምንጭ
-ወላይታ ሶዶ
-ሆሳዕና
-ወራቤ
-ቡታጅራ
-ወልቂጤ
-ሸገር
-ጅማ
-አዳማ
-ሻሸመኔ
-ቢሾፍቱ
-ባቱ
-አምቦ
-መቐለ
-አክሱም
-ዓዲግራት
-ጋምቤላ ከተማ እና
-አሶሳ የሚገኙ የሁሉም ባንክ ደንበኞች ናቸው።
#በተቀሩት የኢትዮጵያ ክፍሎች የሚገኙ የባንክ ቅርንጫፍ ደንበኞች ደግሞ እስከ ሰኔ 30 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ማጠናቀቅ አለባቸው ተብሏል።
#ይሄን በማያደርጉት ላይስ?
በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ሂሳባቸውን የማያስተሳስሩ ደንበኞች የባንክ ሂሳባቸው ከወጪ ወይም ተቀናሽ ግብይት የታገደ (No Debit) ይኾናል።
እገዳው የሚነሳው ደንበኛው የፋይዳ መታወቂያ ቁጥሩን ከባንክ ሂሳብ ቁጥሩ ጋር ሲያስተሳስር ብቻ ይኾናል።
#የተሰጠው አቅጣጫ የዲፕሎማቲክ ማኅበረሰብን እና በውጭ ሀገር የሚኖሩ ነዋሪዎችን አይመለከትም።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleፍትሐዊ የሚዲያ አጠቃቀም ለዴሞክራሲያዊ ምርጫ
Next articleየአማራ ክልል የሰላም እናቶች ለማኅበረሰቡ ሰላም እና ለምርጫው ስኬት እየሠሩ ነው።