አረጋውያን የጥበብ እና የልምድ ምንጮች ናቸው።

5

 

አዲስ አበባ: ግንቦት 04/2018 ዓ.ም (አሚኮ) አረጋውያን በረጅም የሕይወት ዘመናቸው ያካበቱትን የሥነ-ልቦና ጥንካሬ እና የሕይወት ተሞክሮ ለወጣቱ ትውልድ ለማስተላለፍ የሚያስችል የትውልድ ቅብብሎሽ መድረክ በአዲስ አበባ ተካሂዷል።

በመድረኩ ላይ ንግግር ያደረጉት የሴቶች እና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ዴኤታ ሁሪያ አሊ አረጋውያን በማኅበራዊ ጉዳዮች፤ በኢኮኖሚ ልማት፤ በፖለቲካ አመራር እና በሀገር አንድነት ዙሪያ የጎላ ሚና አላቸው ብለዋል።

ከመጽሐፍት ዕውቀት ይልቅ የሕይወት ተሞክሮ ይበልጣል በሚል መርሕ አረጋውያን ለትውልድ ታሪክን፣ ባሕልን እና የሥራ ወዳድነትን በጥበብ እያስተማሩ ይገኛሉ ነው ያሉት።

አረጋውያን የኑሮ ደረጃቸውን እንዲያሻሽሉ እና በሀገር ግንባታ ላይ ያላቸውን አስተዋጽኦ እንዲቀጥሉ ምቹ ሁኔታዎች ሊመቻቹላቸው እንደሚገባ በዚሁ መድረክ ጥሪ ቀርቧል።

“አረጋውያን ላለንባት ኢትዮጵያ የከፈሉት ዋጋ ትልቅ ነው”። ዛሬም እንደ ትናንቱ ለሀገር ሰላም እና አንድነት የጥበብ ምንጭ ኾነው እያገለገሉ ይገኛሉም ብለዋል።

በዚህ መድረክ ከአባት አርበኞች፣ ከምሁራን እና ከጥበብ ሰዎች የሕይወት ተሞከሮ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።

ዘጋቢ፦ ቴዎድሮስ ኃይለ ኢየሱስ

የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ

https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !

Previous articleበከተማዋ የወጣቶችን ተጠቃሚነት ለማሳደግ ውጤታማ ሥራዎች ተከናውነዋል።