
ደሴ: ግንቦት 04/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በደሴ ከተማ “ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር” በሚል መሪ መልዕክት ከወጣቶች ጋር ውይይት ተካሂዷል።
የደሴ ከተማ አሥተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት “ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር” በሚል መሪ መልዕክት ከወጣቶች ጋር የምርጫ እና የሰላም ውይይት አድርጓል።
በመድረኩ የደሴ ከተማ አሥተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ አሸናፊ ዓለማየሁ እንደተናገሩት ነባራዊ ሁኔታን የተረዳ እና በሕገ-መንግሥታዊ የበላይነት የሚያምን ወጣት ለሀገር ዕድገት እና ለሰላም መረጋገጥ ሚናው ከፍተኛ ነው።
ፓርቲው ባለፉት አምስት ዓመታት የወጣቶችን የልማት እና የመልካም አሥተዳደር ጥያቄዎች ለመመለስ አበረታች ሥራዎችን መሥራቱን ጠቅሰው ወጣቶች የአካባቢያቸውን ሰላም በመጠበቅ ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ስኬታማነት እንዲሠሩ ጥሪ አቅርበዋል።
የደሴ ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ሳሙኤል ሞላልኝ በበኩላቸው በከተማዋ የወጣቶችን ተጠቃሚነት ለማሳደግ የተከናወኑ ሥራዎች ውጤታማ መኾናቸውን ገልጸው በቀጣይም የሥራ ዕድል የሚፈጥሩ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ለማስፋፋት በትኩረት እንደሚሠራ አረጋግጠዋል።
ግንቦት 24/2018 ዓ.ም ለሚካሄደው ምርጫ ነዋሪዎች በነቂስ ወጥተው ድምፃቸውን እንዲሰጡም አሳስበዋል።
የውይይቱ ተሳታፊ ወጣቶች በበኩላቸው ምርጫው ሰላማዊ እና ዴሞክራሲያዊ ኾኖ እንዲጠናቀቅ ከጸጥታ ኀይሎች ጋር በመተባበር የድርሻቸውን ለመወጣት እና የከተማቸውን ዕድገት ያፋጥናል ያሉትን ፓርቲ ለመምረጥ ዝግጁ መኾናቸውንም ገልጸዋል።
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ
https://linktr.ee/Amharamediacorporations
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !
