በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ በኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት ዘርፉ የነበሩ ችግሮች እየተፈቱ ነው።

8

 

ደሴ: ግንቦት 04/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የኮምቦልቻ ከተማ አሥተዳደር ኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት መምሪያ” ኢትዮጵያ ታምርት እኛም እንሸምት” የንቅናቄ መድረክ አካሂዷል።

በመድረኩ የአማራ ክልል ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬን ጨምሮ ሌሎች የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል።

በመርሐ ግብሩ ላይ የተሳተፉ አልሚ ባለሀብቶች ከተማ አሥተዳደሩ በኢትዮጵያ ታምርት እኛም እንሸምት ንቅናቄ ለአምራች ዘርፉ በሰጠው ትኩረት ከዚህ ቀደም የነበሩ ችግሮች እየተቀረፉ መጥተዋል ብለዋል።

የኮምቦልቻ ከተማ አሥተዳደር ኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት መምሪያ ኀላፊ ሁሴን ሙሄ በበጀት ዓመቱ ከ8 ፋብሪካዎች 44 ሚሊዮን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሬ ማግኘት እንደተቻለ ገልጸዋል።

የኮምቦልቻ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ መሐመድ አሚን የሱፍ ሀገር ለመለወጥ በኢንቨስትመንት መስኩ ላይ ትኩረት ማድረግ እንደሚገባ ተናግረዋል። አልሚዎች በሀገራቸው ላይ ኢንቨስት እንዲያደርጉም ጥሪ አቅርበዋል።

ኮምቦልቻ ከተማን ለኢንቨስትመንት እና ለአምራች ዘርፉ የተመቸ ለማድረግ ከተማ አሥተዳደሩ በትኩረት እየሠራ መኾኑንም አመላክተዋል።

የአማራ ክልል ኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኀላፊ እንድሪስ አብዱ ባለፉት አራት ዓመታት በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ከ64 ሺህ በላይ ለሚኾኑ ዜጎች ቋሚ የሥራ ዕድል ተፈጥሯል ብለዋል።

የአገልግሎት ዘርፉን በዲጂታል የታገዘ ለማድረግ በትኩረት እየተሠራ እንደሚገኝም ገልጸዋል። በዘርፉ የሚታዩ ችግሮችን ለመቅረፍ ክልሉ ከ567 ሚሊዮን ብር በላይ ወጭ አድርጓል ነው ያሉት።

ከተማ አሥተዳደሩ “በኢትዮጵያ ታምርት እኛም እንሸምት” ንቅናቄ የተገነቡ የቆርቆሮ ማምረቻ እና የዘይት ፋብሪካዎችን መርቆ ለአገልግሎት ክፍት ማድረጉም ተመላክቷል።

ዘጋቢ፦ ፊኒክስ ኃየሎም

የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ

https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !

Previous articleየክልሉን ሰላም በአስተማማኝ ደረጃ ለመጠበቅ የሚያስችል የሚሊሻ ኀይል እየተገነባ ነው።
Next articleአዲስ አበባ ከተማ በአጭር ጊዜ ውስጥ በከተማ ማደስ እና ማስዋብ ከፍተኛ ለውጥ ማምጣት ችላለች።