
ባሕር ዳር፡ ግንቦት 04/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባስተላለፉት መልእክት በፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ እና በፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በጋራ አዘጋጅነት በኬንያ ናይሮቢ በተካሄደው የአፍሪካ ፎርዋርድ ጉባኤ የኢትዮጵያን ተሞክሮ አካፍያለሁ ብለዋል።
በተለይም የአረንጓዴ ኢንዱስትሪ ልማት እና የኃይል ሽግግርን በተመለከተው ውይይት መድረክ ላይ ከተሞክሯችን የተቀዱ ከፍ ያሉ ሀሳቦች ተነስተዋል። ኢትዮጵያ በተነሱት ሁለት ዘርፎች የጀመረችውን ስራ በማጠናከር የላቀ ሚና መጫወቷን ትቀጥላለች ነው ያሉት።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
