
ደብረ ብርሃን: ግንቦት 04/2018 ዓ.ም (አሚኮ)የሰሜን ሸዋ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት “ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር” በሚል መሪ መልዕክት የምረጡኝ ቅስቀሳ እና የምልክት ማስተዋወቅ መርሐ ግብር አካሂዷል።
የሰሜን ሸዋ ዞን ዋና አሥተዳዳሪ መካሻ ዓለማየሁ ብልጽግና ፓርቲ ግልጽ ራዕይ፣ ጠንካራ አባላት እና መሪ ያለው ነው ብለዋል። የሕዝቡን የኑሮ ሁኔታ ለማሻሻል ሌት ከቀን የሚተጋ ፓርቲ መኾኑንም ገልጸዋል።
ብልጽግና ፓርቲ የጽናት ትክክለኛ ማሳያ እና ተምሳሌት መኾኑንም አስገንዝበዋል።
ምርጫው ሰላማዊ ኾኖ እንዲጠናቀቅ እና ለጋራ ሀገር ግንባታ እንዲውል ፓርቲው ቁርጠኛ መኾኑን ነው የተናገሩት። ድህነትን ለማጥፋት ምርታማነትን ማሳደግ እና ግብርናን ማዘመን ላይ ትኩረት ተሰጥቶ እየሠራ መኾኑን አንስተዋል።
የሰሜን ሸዋ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ኤሊያስ አበበ ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ዴሞክራሲያዊ፣ ፍትሐዊ፣ ሰላማዊ እንዲኾን እና ለተፎካካሪ ፓርቲዎች ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር እየተሠራ መኾኑን ተናግረዋል።
የዴሞክራሲ ሥርዓትን ለመገንባት ብልጽግና ፓርቲ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሠራም ገልጸዋል።
የመድረኩ ተሳታፊዎችም ማኅበረሰቡ ይበጀኛል የሚለውን ፓርቲ መምረጥ እንዳለበት ገልጸዋል።
የፓርቲዎችን የምርጫ ቅስቀሳ እና አማራጭ ሃሳብ በማመዛዘን የኢትዮጵያን የዴሞክራሲ ጉዞ ለሚያፋጥን ፓርቲ ድምጻቸውን እንደሚሰጡም ተናግረዋል።
ዘጋቢ፦ ስንታየሁ ሀይሉ
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ
https://linktr.ee/Amharamediacorporations
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !
