
ባሕር ዳር: ግንቦት 04/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በኢትዮጵያ 7ኛው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ ግንቦት 24/2018 ዓ.ም ይካሄዳል። ተፎካካሪ ፓርቲዎችም ለምርጫው ዝግጅት እያደረጉ ይገኛሉ። የምርጫው ሂደት ሰላማዊ፣ ነፃ፣ ፍትሐዊ እና ታማኒ እንዲኾን የፖለቲካ ፓርቲዎች ኀላፊነታቸውን መወጣት ይኖርባቸዋል።
በባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካል ሳይንስ እና ዓለም አቀፍ ጥናት ትምህርት ክፍል መምህር መሀመድ ይማም (ዶ.ር) ምርጫ ሀገረ መንግሥት የሚመሠረትበት፣ ሕዝብ መብቱን የሚያረጋግጥበት መኾኑን ገልጸዋል።
በምርጫ ወቅት የፖለቲካ ፓርቲዎች ለሕዝብ ይዘው የቀረቡትን ሀሳብ በአግባቡ በማስተዋወቅ እንደሚፈተሹ ገልጸዋል። መራጩ ሕዝብም ይወክለኛል ያለውን ፓርቲ የሚመርጥበት ነው ብለዋል። ዶክተር መሀመድ እንዳሉት የምርጫው ሂደት ቅቡልነት ያለው እንዲሆን የፖለቲካ ፓርቲዎች ኀላፊነት ከፍተኛ ነው።
ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎችም ለሕዝብ እና ለሀገር የሚበጁ አማራጭ ሀሳቦችን እና ፖሊሲዎችን ይዘው በመቅረብ ማስተዋወቅ እንዳለባቸው አብራርተዋል።
የምርጫው ሂደት በሰለጠነ መንገድ እንዲከወን “ድምፄ ዋጋ አለው “በማለት ህዝቡም ድምጹን መስጠት እንዳለበትም አስገንዝበዋል።
ምርጫ የዴሞክራሲ ምህዳር ልምምድ የሚደረግበት በመኾኑ ለሰላማዊነቱ ሁሉም ዜጋ የድርሻውን መወጣት እንዳለበትም ተናግረዋል። ጤናማ የምርጫ ሥርዓት ለማካሄድ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሕግ እና ሥርዓትን መከተል እንደሚገባቸውም ገልጸዋል።
ዶክተር መሀመድ የፖለቲካ ፓርቲዎች በምርጫ ወቅት መራጩ ሕዝብ የሚሰጣቸውን ውጤት አምነው መቀበል እንዳለባቸው ተናግረዋል። መራጮችም የምርጫ ካርዳቸውን በአግባቡ በመያዝ፣ ለሚወክላቸው ፓርቲ ድምጻቸውን መስጠት እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል።
#Ethiopia #Election2018 #Democracy #BahirDarUniversity #PeacefulElection
ዘጋቢ ፦ ሥራውድንቅ ደሳለው
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/Amharamediacorporations
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
