
ገንዳውኃ፡ግንቦት 03/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የምዕራብ ጎንደር ዞን የመንግሥት ሠራተኞች እና የብልጽግና ፓርቲ አባላት “ጠንካራ አደረጃጀት ለተሳካ ምርጫ” በሚል መሪ መልዕክት በገንዳውኃ ከተማ ተወያይተዋል።
ሀገርን ሊያስቀጥል የሚችል ጠንካራ ፓርቲ ለመገንባት ሥራን ቆጥሮ መሥራት እና ሰብዓዊነትን ማስቀደም እንደሚገባም አባላቱ ገልጸዋል።
ሰባተኛውን ጠቅላላ ምርጫ ስኬታማ ለማድረግ የቅድመ ዝግጅት እና የቅስቀሳ ተግባራትን አጠናክረው እንደሚያስቀጥሉም ተናግረዋል።
ምርጫው ዴሞክራሲያዊ፣ ፍትሐዊ እና ተዓማኒ ኾኖ እንዲጠናቀቅ የበኩላቸውን ድርሻ እንደሚወጡም ገልጸዋል።
የምዕራብ ጎንደር ዞን የሲቪል ሰርቪስ እና የሰው ሃብት ልማት መምሪያ ኀላፊ ነጋ ከፋለ የምርጫው ሂደት በዕውቀት እና በሠለጠነ መንገድ እንዲመራ ምሁራን ያላቸውን ሚና እንዲያጠናክሩ አስገንዝበዋል።
የምዕራብ ጎንደር ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ እንዳለው ማሩ ምርጫው ሰላማዊ እና ዴሞክራሲያዊ ኾኖ በስኬት እንዲጠናቀቅ በትኩረት እየተሠራ መኾኑንም ተናግረዋል።
ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊ በኾነ መንገድ እንዲካሄድ ምቹ ሁኔታን መፍጠር ከአባላቱ የሚጠበቅ ተግባር ነው ብለዋል።
የአማራ ክልል የርእሰ መሥተዳድሩ የአሥተዳደር ጉዳዮች አማካሪ ጥላሁን መኳንንት የክልሉ መንግሥት ለምርጫው ሰላማዊ እና ስኬታማ መኾን አስፈላጊውን ክትትል እያደረገ መኾኑን ተናግረዋል።
በዞኑ እየተከናወኑ ያሉ የምርጫ ቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ትኩረት ሊሰጣቸው እና ሊጠናክሩ እንደሚገባ መልዕክት አስተላልፈዋል።
#7ኛው_ምርጫ #ገንዳውኃ #ኢትዮጵያ
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ
https://linktr.ee/Amharamediacorporations
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !
