“አዲስ አበባ ለሕጻናት የምትመች ከተማ እየኾነች ነው” ከንቲባ አዳነች አቤቤ

4

 

አዲስ አበባ: ግንቦት 03/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የአዲስ ዓለም አቀፍ የቀደማይ ልጅነት ኮንፈረንስ በአዲስ አበባ ተጀምሯል።

በኮንፈረንሱ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከተማዋ ይህንን ዓለም አቀፍ ኮንፈረንስ ለማዘጋጀት ዕድል በማግኘቷ አመሥግነዋል።

አዲስ አበባ ሕጻናትን ለማሳደግ ምቹ እናደርጋታለን ባልነው መሠረት ስኬታማ ሥራዎችን አከናውነናል ብለዋል። በዚህም 5ሺህ የሕጻናት መጫዎቻዎች እና 1ሺህ 100 የሕጻናት አንክብካቤ ማዕከላትን ገንብተናል ነው ያሉት።

የመኖሪያ አካባቢዎች ለሕጻናት ምቹ እንዲኾኑ በኮሪደር ልማቱ መሥራታቸውንም አስገንዝበዋል።

ለቀዳማዊ ልጅነት ልዩ ትኩረት በመስጠት የአንደኛ ደረጃ ትምሀረት ቤቶች ምቹነት 92 በመቶ እንዲደርስ ማድረግ መቻሉን ጠቅሰዋል።

ተግባሩን ተቋማዊ አድርጎ ለማስቀጠል የአፍሪካ የቀዳማዊ ልጅነትን በማቋቋም ለሀገር የልህቀት ማዕከል አንዲኾን ማድረግ ተችሏልም ብለዋል።

የአፍሪካ ቀዳማይ ልጅነት ማዕከል ሥራ አሥፈጻሚ ከበደ ወርቁ ቀዳማይ ልጅነት ተግባራዊ ውጤት ያለው ኾኖ አንዲቀጥል መንግሥታት፣ ማኅበረሰቡ እና ዓለም አቀፍ አጋር ተቋማት በኢንቨስትመንት እና በፖሊሲ ላይ ልዩ ትኩረት ሰጥተው እንዲሠሩ ጥሪ አቅርበዋል።

ዘጋቢ፦ አንዱዓለም መናን

#የቀዳማይ_ልጅነት #አዲስአበባ #ኢትዮጵያ

የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ

https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !

Previous article“ለመራጭነት ብቻ ሳይሆን ለሰላማዊ ምርጫም አርአያ እንሆናለን” የመንግሥት ሠራተኞች
Next articleብልጽግና የሐሳብ እና የተግባር ባለቤት ነው።