ብልጽግና የሐሳብ እና የተግባር ባለቤት ነው።

4

 

ደብረታቦር፡ግንቦት 03/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በደቡብ ጎንደር ዞን የፋርጣ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የምርጫ ቅስቀሳ አካሂዷል።

በመድረኩ ላይ የተገኙት የፓርቲው መሪዎች እና አባላት ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ፍትሐዊ እና ስኬታማ ኾኖ እንዲጠናቀቅ የድርሻቸውን እንደሚወጡ ተናግረዋል።

የፋርጣ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ አማረ ይሁኔ ብልጽግና ፓርቲ የሀገሪቱን የዕድገት ጉዞ እያፋጠነ ያለ ፓርቲ ነው ብለዋል።

ፓርቲው የፖለቲካ ምህዳሩን በማስፋት እየሠራ መኾኑን ጠቅሰዋል። በቀጣይም ኢትዮጵያን ተምሳሌታዊ ሀገር ለማድረግ በቁርጠኝነት እንደሚሠራ ገልጸዋል።

የፋርጣ ወረዳ ዋና አሥተዳዳሪ ይርጋ ጌትነት ፓርቲው ለዴሞክራሲ ግንባታ ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ መኾኑን ተናግረዋል። ለሰላም ግንባታም የብሔራዊ ምክክር ኮሚሽንን ተግባራት እየደገፈ እንደሚገኝ አስረድተዋል።

ፓርቲው የገባውን የልማት ቃል በተግባር እንደሚያሳይ ተናግረዋል። በተለይም ግብርናውን በማዘመን እና ሰው ሠራሽ ማዳበሪያ ፋብሪካን በአጭር ጊዜ በማጠናቀቅ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እንደሚሠራ አንስተዋል።

የደቡብ ጎንደር ዞን ማዕድን መምሪያ ኀላፊ ብርቄ ፀጋ ብልጽግና የሐሳብ እና የተግባር ባለቤት መኾኑን ገልጸዋል። ፓርቲው ባለፉት ዓመታት ያከናወናቸውን ተግባራት ለማኅበረሰቡ ግንዛቤ መፍጠር እንደሚገባ አሳስበዋል።

ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ነጻ፣ ፍትሐዊ እና ዴሞክራሲያዊ በኾነ መንገድ እንዲከናወን የሁሉንም ርብርብ እንደሚጠይቅም አስገንዝበዋል።

#7ኛው_ምርጫ #ደብረታቦር #ኢትዮጵያ

የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ

https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !

Previous article“አዲስ አበባ ለሕጻናት የምትመች ከተማ እየኾነች ነው” ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Next articleየበርበሬ አምራቾች የኪሳራ ስጋት እና የምርምር ተስፋዎች