
አዲስ አበባ: ግንቦት 03/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የአዲስ ዓለም አቀፍ የቀደማይ ልጅነት ኮንፈረንስ በአዲስ አበባ ተጀምሯል።
በኮንፈረንሱ ላይ የተገኙት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ኢትዮጵያ ለቀዳማዊ ልጅነት ልዩ ትኩረት ትሰጣለች ብለዋል።
በዚህም የራሱን አዋጅ በመቅረጽ በትምህርት ፓሊሲ ጭምር በማካተት በትኩረት እየተሠራ እንደኾነ ጠቁመዋል።
ኢትዮጵያ ለቀዳማዊ ልጅነት ትኩረት ሰጥታለች ሲባል የሰው ተኮር ፕሮጀክቶች አካል ማድረግ እንደተቻለ የሚያሳይ መኾኑን አብራርተዋል።
ሀገር የምትሠራው በልጆች ላይ በሚሠራ ተግባር በመኾኑ ኢትዮጵያ በልጆች ላይ ልዩ ትኩረት ሰጥታ እየሠራች ነው ብለዋል። ኢትዮጵያ በኮሪደር ልማት ለሕጻናት ምቹ የኾኑ ስፍራዎች እንዲገነቡ እያደረገች መኾኗን አስረድተዋል።
ሕጻናት በሌማት ትሩፋት የተመጣጠነ ምግብ እንዲያገኙ እና ሁሉም የመንግሥት ተቋማት የሕጻናት ማቆያ እንዲገነቡ እየተደረገ መኾኑን ገልጸዋል።
35 ሺህ የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምሀርት ቤቶች እየተገነቡ መኾናቸውን አንስተዋል።
በሰቆጣ ቃል ኪዳን ውስጥ ኢትዮጵያ በ2022 ከሁለት ዓመት በታች ያሉ ሕጻናት መቀንጨርን ዜሮ ለማድረግ እየሠራች እንደኾነም አስገንዝበዋል።
ዘጋቢ:- አንዱዓለም መናን
#የቀዳማይ_ልጅነት #አማራክልል #ኢትዮጵያ
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ
https://linktr.ee/Amharamediacorporations
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !
