
ደሴ: ግንቦት 03/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የደሴ ከተማ አሥተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የመንግሥት ሠራተኛ አባላት የቅስቀሳ እና እጩዎችን የማስተዋወቅ መርሐግብር እያካሄደ ነው።
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል እና በደሴ ከተማ የብልጽግና ፓርቲ እጩ ተወዳዳሪ ማኅተመ ኃይሌ (ዶ.ር) ብልጽግና ፓርቲ ኅብረ ብሔራዊ አንድነትን ለማጽናት እና ሀገርን ለመገንባት አልሞ እየሠራ ያለ ፓርቲ ነው ብለዋል።
የደሴ ከተማ አሥተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ አሸናፊ ዓለማየሁ ሰላምን፣ ዴሞክራሲን እና ልማትን ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት አባላቱ ላደረጉት ርብርብ አመሥግነዋል።
ዜጎች በነፃነት እንዲመርጡ ምቹ ሁኔታ መፈጠሩንም አስረድተዋል።
የደሴ ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ሳሙኤል ሞላልኝ ብልጽግና ፓርቲ የብሔርተኝነት፤ የኢኮኖሚ እና የማኀበራዊ ስብራትን በመጠገን እየሠራ መኾኑን ጠቁመዋል። ፓርቲው ሀገርን ከመፍረስ ያዳነ ነውም ብለዋል።
ብልጽግና ፓርቲ ያለፈ ሥርዓትን የሚያጣጥል ሳይኾን መልካም ሥራዎችን ወስዶ እንደ እርሾ በመጠቀም የሚሠራ መኾኑንም አመላክተዋል።
ዘጋቢ፦ ሳሙኤል ኪሮስ
#7ኛው_ምርጫ #ደሴ #ኢትዮጵያ
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ
https://linktr.ee/Amharamediacorporations
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !
