ምርጫ የአስተማማኝ ሰላም ማረጋገጫ ነው።

5

 

ፍኖተ ሰላም: 02/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የምዕራብ ጎጃም ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ከጃቢ ጠህናን ወረዳ እና ፍኖተ ሰላም ከተማ ጋር በጋራ በመኾን 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ አስመልክቶ የምርጫ ቅስቀሳ፣ የምልክት ማስተዋወቅ እና የድጋፍ ሰልፍ በፍኖተ ሰላም እያተካሄደ ነው።

መርሐ ግብሩ የዞን፣ የፍኖተ ሰላም ከተማ እና የጃቢ ጠህናን አመራሮች የፓርቲው አባላት እና ደጋፊዎች በተገኙበት ”ኢትዮጵያ ወደ ተምሳሌት ሀገር” በሚል መሪ ሐሳብ ነው እየተካሄደ ያለው።

የፍኖተ ሰላም ከተማ አሥተዳደር ምክትል ከንቲባ ጊዜው ደግአረገ ብልጽግና ፓርቲ ታላላቅ ሀገራዊ ፕሮጀክቶችን በማከናወን የሕዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየተጋ መኾኑን ተናግረዋል።

በብልጽግና ፓርቲ የምዕራብ ጎጃም ዞን ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ዓባይ ዓለሙ የኢትዮጵያውያን የዘመናት የዴሞክራሲ ጥያቄ ምላሽ የሚያገኘው ስኬታማ የምርጫ ሂደት ማካሄድ ሲቻል ነው ብለዋል።

ፓርቲው ካለፉት የምርጫ ጉድለቶች ሁሉ ትምህርቶችን በመውሰድ 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ዴሞክራሲያዊ እና ተዓማኒነትን በተሞላ መንገድ እንዲካሄድ እየተሠራ ነው ብለዋል።

ምርጫውን በስኬት ማጠናቀቅ ሁለንተናዊ ብልጽግናን ለማሳለጥ ወሳኝነት እንዳለውም አንስተዋል።

የምዕራብ ጎጃም ዞን ዋና አሥተዳዳሪ እድሜዓለም አንተነህ ብልጽግና ፓርቲ የትናንት ችግሮችን በማከም ዘላቂ ልማትን ለማምጣት እየሠራ ያለ ፓርቲ ነው ብለዋል።

ምርጫ የሕጋዊ መንግሥት መመስረቻ ቁልፍ መሳሪያ ነው ብለዋል። በተለይ የአስተማማኝ ሰላም ማረጋገጫ መኾኑንም ነው የተናገሩት።

በዞኑ በመገንባት ላይ ያሉ ታላላቅ ፕሮጀክቶች እንዲጠናቀቁ ምርጫውን በስኬት ማጠናቀቅ ወሳኝነት እንዳለው ገልጸዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ሚሊሻ የማኅበረሰቡ የሰላም ምሰሶ ነው” ኮሚሽነር አስቻለ አላምሬ
Next articleምክንያታዊ ወጣቶች ለውጤታማ ምርጫ!