
ደብረ ታቦር: ግንቦት 02/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በደብረ ታቦር ከተማ አሥተዳደር በብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የመወዳደሪያ ምልክት እና የእጩዎች ትውውቅ የፓርቲው አባላት እና ደጋፊዎች በተገኙበት የጎዳና ላይ ሰልፍ አካሂደዋል።
ፕሮግራም ላይ የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች፣ የደብረ ታቦር ከተማ እና የደቡብ ጎንደር ዞን ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል።
የአማራ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ኀላፊ ኢብራሂም ሙሐመድ (ዶ.ር) ምርጫ
የሠለጠነ ሕዝብ መገለጫ ነው ብለዋል። 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ በስኬት ለማከናወን ሕዝቡ በጥንቃቄ እና በመረጃ ላይ ተመስርቶ ድምፁን በመስጠት እንዳለበት ገልጸዋል።
ምርጫው ነፃና ፍትሐዊ ኾኖ እንዲጠናቀቅ ፓርቲያቸው ብልጽግና አብክሮ እየሠራ ይገኛል ያሉት ደግሞ የደብረ ታቦር ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ ደሴ መኮንን ናቸው።
ባለፉት የሥራ ዘመናት መሠረታዊ ለውጦች ማከናወን መቻሉንም አስታውሰዋል።
ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ፣ የኮሪደር ልማት እና ትልልቅ ሀገራዊ ፕሮጀክቶች በስኬት ተከናውነዋል ብለዋል።
ፓርቲያቸው ብልጽግና ሀገራዊ ምርጫውን ካሸነፈ የኢትዮጵያ የህልውና ጉዳይ የኾነውን የባሕር በር ጥያቄ በሰላማዊ መንገድ እልባት ለማሰጠት በፅኑ እንደሚሠሩ ገልጸዋል።
የደብረ ታቦር ከተማ አሥተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ደበበ አክሎግ በሀገሪቱ ያሉ ጸጋዎችን ለይቶ በማወቅ በሥራ እድል ፈጠራ እና በኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ረገድ የተገኘው ስኬት እጅግ የሚያኮራ ነበር ብለዋል።
ብልጽግና ፓርቲ ሀገራዊ ምርጫውን ካሸነፈ ኢትዮጵያን የአፍሪካ ዋነኛ የቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ እንደሚሠሩ ገልጸዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
