መሪን በካርድ መምረጥ ብልህነት ነው።

3

 

ገንዳ ውኃ: ግንቦት 02/2018 ዓ.ም (ዓ.ም) በምዕራብ ጎንደር ዞን በገንዳ ውኃ ከተማ ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የብልጽግና ፓርቲ የይምረጡኝ ቅስቀሳ ተካሂዷል። ፓርቲው ዕጩ ተወዳዳሪዎችንም አስተዋውቋል።

የምዕራብ ጎንደር ዞን ዋና አሥተዳዳሪ እያሱ ይላቅ ብልጽግና ፓርቲ ከለውጡ ዓመታት ወዲህ በተግባር የሚታዩ እና የሚጨበጡ በርካታ ሥራዎችን መሥራቱን ተናግረዋል።

ፓርቲው የልማት እና የፖለቲካ ጥያቄዎችን ሲፈታ የቆየ መኾኑን ዋና አሥተዳዳሪው ገልጸው ሀገሪቷን ወደ ተሻለ የዕድገት ደረጃ ከፍ ለማድረግ እየሠራ ያለ ፓርቲ ነው ብለዋል። ሰላምን ለማስከብርም እየተሠራ ስለመኾኑ ጠቁመዋል።

የሀገሪቱ የህልውና ጉዳይ የኾነውን የባሕር በር ጥያቄ በሰላማዊ እና በዲፕሎማሲያዊ መንገድ የሚፈታ ፓርቲ ነው ብለዋል።

በምርጫ ካርድ ሰላማዊ በኾነ መንገድ መሪን መምረጥ ብልህነት መኾኑን ገልጸዋል።

ብልጽግና ፓርቲ ትልልቅ ሀገራዊ ፕሮጀክቶችን የሚሠራ እና ሠርቶ በተግባር የሚያሳ ነው ያሉት ደግሞ የምዕራብ ጎንደር ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ እንዳለው ማሩ ናቸው።

ሀገሪቱን በቱሪዝም እና በሌሎች ዘርፎች በማሳደግ ከሌሎች ሀገራት እኩል እንድታድግ የሚሠራ ፓርቲ ነው ብለዋል።

የገንዳ ውኃ ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አብዱከሪም ሙሐመድ ብልጽግናን ከመረጡ በቀጣይ አምስት ዓመታት በርካታ መሠረተ ልማቶች የሚሠራ ፓርቲ መኾኑን ተናግረዋል። ሀገርን የሚያስቀጥል እና ዕድገትን የሚያፋጥን ፓርቲ መኾኑንም አመላክተዋል።

ብልጽግና ሰላምን የሚሰብክ፣ የሚያሰፍን እና ድህነትን የሚያስቀር ፓርቲ መኾኑንም አመላክተዋል።

ብልጽግና የሀገርን ልማት የሚያፋጥን እና ሰላምን ለማስከበር እየሠራ ያለ ፓርቲ መኾኑን የድጋፍ ሰልፈኞች አንስተዋል። ብልጽግናን ለመምረጥም ዝግጁ መኾናቸውን ተናግረዋል።

7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊ፣ ነፃ እና ፍትሐዊ ኾኖ እንዲካሄድ ኀላፊነታቸውን እንደሚወጡ ሰልፈኞች ተናግረዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየአማራ ክልል ሚሊሻ ኮሚሽን የ30ኛ ዓመት የሚሊሻ ምስረታ በዓልን በቡልጋ ከተማ እያከበረ ነው።
Next articleምርጫ የሥልጡን ሕዝብ መገለጫ ነው።