
ደብረ ብርሃን: ግንቦት 02/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ሚሊሻ ኮሚሽን እና የሰሜን ሸዋ ዞን ሚሊሻ መምሪያ 30ኛ ዓመት የሚሊሻ ምስረታ በዓል በቡልጋ ከተማ እየተከበረ ይገኛል።
በበዓሉ አከባበር ላይ ከፍተኛ የክልል እና የዞን የሥራ ኀላፊዎች፣ የጸጥታ አካላት እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
በዕለቱም በሚሊሻ አባላት የተለያዩ ወታደራዊ ትርኢቶች የቀረቡ ሲኾን ለሀገርና ለሕዝብ ደኅንነት ሲባል የተከናወኑ ተግባራትም ተዘክረዋል።
የሚሊሻ አባላት ባለፉት ሦስት አሥርት ዓመታት የሕዝብን ሰላም በማስከበር እና በልማት ሥራዎች ላይ ያበረከቱት አስተዋጽኦ በዝግጅቱ ላይ ትኩረት ተሰጥቶታል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
