
ባሕር ዳር: ግንቦት 02/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን የዩክሬን ጦርነት ሊያበቃ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥተዋል።
ፕሬዝዳንቱ ዘላቂ የሰላም ስምምነት ከተረቀቀ በሦሥተኛው ሀገር ከቮሎዲሚር ዘለንስኪ ጋር ለመገናኘት ፈቃደኛ መኾናቸውን አልጀዚራ አረጋግጧል። ይህ አስተያየት የተሰጠው ሩሲያና ዩክሬን ለሦሥት ቀናት የተኩስ አቁም ለማድረግ እና ሺህ እስረኞችን ለመለዋወጥ ከተስማሙ በኋላ ነው።
ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሁለቱ ሀገራት የተኩስ አቁም ጥያቄያቸውን በመቀበላቸው የሰላም ድርድሩ መቃረቡን ገልጸዋል።
ፑቲን ከዘለንስኪ ጋር የሚኖረው ግንኙነት ለድርድር ሳይኾን የተጠናቀቀን ስምምነት ለማፅደቅ ብቻ መኾን እንዳለበት አጽንኦት ሰጥተዋል።
ለዓመታት የዘለቀው ይህ ጦርነት በሩሲያ ኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ ጫና አሳድሯል። ሞስኮ አሁንም ከዩክሬን ግዛት ሲሶ ያነሰውን ክፍል ከመቆጣጠር ያለፈ ድል አላሳካችም።
ፑቲን ከአውሮፓ ጋር ስለ ወደፊቱ የጸጥታ ሁኔታ ለመወያየት ያላቸውን ፍላጎት ቢገልጹም ለንግግር የሚመርጡት ግን የቀድሞውን የጀርመን ቻንስለር ጌርሃርድ ሽሮደርን መኾኑን ጠቁመዋል።
ዘጋቢ:- ስማቸው አጥናፍ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
