የዛሬ ወጣቶች ድምፅ የነገዋን ኢትዮጵያ እውን ያደርጋል።

7

 

ባሕር ዳር: ግንቦት 02/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በምርጫ የዛሬ ወጣቶች ድምፅ ተሳትፎ እና ውሳኔ የነገን ሀገር እድገት እንደሚወስን ይታመናል። በኢትዮጵያ ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ግንቦት ወር እንደሚካሄድ ይታወቃል።

የአማራ ክልል ወጣቶች ማኅበራት ፌደሬሽን ፕሬዝዳንት ግርማ አቸነፍ የዛሬ ወጣቶች ድምፅ የነገዋን ሀገር አቅጣጫ የሚያስቀምጥ እንደኾነ ይገለጻሉ። ለዚህም ወጣቶች በምርጫ ሂደት ሲሳተፉ የራሳቸውን እና የሀገራቸውን የወደፊት ሕልውና ይወስናሉ። ፕሬዝዳንቱ እንዳሉት ወጣቶች በተፎካካሪ ፓርቲዎች የሚቀርቡ ኘሮግራሞችን በመከታተል በዕውቀት እና በትክክለኛ መረጃ ላይ ተመስርተው ይበጀኛል የሚሉትን ፓርቲ እንዲመርጡ ከላይ እስከ ታች ድረስ የግንዛቤ ፈጠራ ተሠርቷል ብለዋል። የዴምክራሲ ሥርዓት በወጣቶች እንዲገነባ ጥረት መደረጉን ነው ያነሱት።

በምርጫ የዛሬ ወጣቶች ድምፅ የነገዋን ኢትዮጵያ እውን ያደርጋል ያሉት አቶ ግርማ ይወክለኛል የሚሉትን ፓርቲ በፍትሐዊ መንገድ መምረጥ እንዲችሉ መሠራቱን ነው የገለጹት።

ፌደሬሽኑ ለሚካሄደው ጠቅላላ ምርጫ 541 ታዛቢዎች እና 88 አስተባባሪ ወጣቶች አባላት እንዲሳተፉ ዝግጅት መደረጉን ተናግረዋል። ምርጫው ሰላማዊ ኾኖ እንዲጠናቅ ወጣቶች የድርሻቸውን እንዲወጡ መሠራቱንም አንስተዋል።

እንደ አቶ ግርማ ገለጻ ወጣቶች ባልተፈለገ ኘሮፖጋንዳ ተገዢ እንዳይኾኑ እና እንዳይጠለፉ ሥራዎች ተሠርተዋል ነው ያሉት። ከማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲ ነፃ እና ገለልተኛ ኾነው ተግባራትን መሥራት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።

ፌዴሬሽኑ ከ3 ነጥብ 2 ሚሊዮን በላይ የሚኾኑ ወጣቶች አባላት ቢኖሩትም ከፌዴሬሽኑ አደረጃጀት ውጭ ለኾኑ ወጣቶች ጭምር የግንዛቤ ፈጠራ ሥራ መሠራቱን ነው የገለጹት።

የወጣቶች ድርሻ ከፍተኛ መኾኑን ያነሱት አቶ ግርማ ሰላማዊ እና ዴሞክራሲያዊ ምርጫ እንዲከወን ከሌሎች አካላት ጋር በቅንጅት የበኩላቸውአሻራ እንዲያስቀምጡ እየተሠራ ነው ብለዋል።

ወጣቶች በየአካባቢያቸው በሰከነ መንገድ ምርጫው ሰላማዊ ኾኖ እንዲጠናቀቅ መሥራት እንዳለባቸው ጥሪ አቅርበዋል።

ዘጋቢ፦ሥራውድንቅ ደሳለው

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየአማራ ክልል ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች በሰሜን ወሎ ዞን ራያ ቆቦ ወረዳ የልማት ሥራዎችን ጎበኙ።
Next article“ባለፉት ዓመታት ከተፈጠሩ የሥራ ዕድሎች ውስጥ 51 በመቶው ሴቶችን ተጠቃሚ ያደረጉ ናቸው” ከንቲባ አዳነች አቤቤ