የአማራ ክልል ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች በሰሜን ወሎ ዞን ራያ ቆቦ ወረዳ የልማት ሥራዎችን ጎበኙ።

3

 

ባሕር ዳር: ግንቦት 01/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች በሰሜን ወሎ ዞን ራያ ቆቦ ወረዳ በአራዶም አካባቢ እየለማ የሚገኘውን የማንጎ ኩታገጠም ጎብኝተዋል።

በጉብኝቱ የአማራ ክልል ምክትል ርእሰ መሥተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ.ር)፣ የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኀላፊ ፍስሐ ደሳለኝ እና ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል።

የማንጎ ኩታገጠሙ በ415 ሄክታር መሬት ላይ እየለማ የሚገኝ ነው። ከማንጎ ልማቱ በተጨማሪ የፓፓያ ተክልም እየለማ ነው።

በኩታገጠሙ ልማት የችግኝ ጣቢያ ይገኛል። በችግኝ ጣቢያው ለኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ እና ለደን ልማት የሚውሉ የተለያዩ ችግኞች እየለሙ ይገኛሉ።

የራያ ቆቦ ወረዳ በእንስሳት ሃብቷ እና በማሽላ ምርቷ ትታወቃለች።

ዘጋቢ:- ያየህ ፈንቴ

የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ

https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !

Previous article” ልማታችንን የሚያስቆመን ኃይል የለም” አብዱ ሁሴን (ዶ.ር)