“ብልጽግና ፓርቲ ከችግር በላይ ኾኖ የሠራ ፓርቲ ነው” አብዱ ሁሴን (ዶ.ር)

1

 

ባሕር ዳር: ግንቦት 01/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች በሰሜን ወሎ ዞን ራያ ቆቦ የምርጫ ቅስቀሳ አካሂደዋል።

የሰሜን ወሎ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ከድር ሙስጦፋ በቀጣይ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነትን፤ ሰላምን እና የተሻለ ልማትን ለማግኘት ብልጽግናን እንዲመርጡ ጠይቀዋል።

የሰሜን ወሎ ዞን ዋና አሥተዳዳሪ አራጌ ይመር ብልጽግናን መምረጥ ሀገርን ማስቀጠል፤ ድህነት፣ ኋላቀርነትን ማስቀረት እና አፍሪካዊ ተምሳሌትነትን ማስቀጠል ነው ብለዋል።

ብልጽግና የተለያዩ ፕሮጀክቶችን እየገነባ እና የሀገርን እድገት እያሳደገ እንደሚገኝም ጠቁመዋል።

የአማራ ክልል ምክትል ርእሰ መሥተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ.ር) ብልጽግና ትናንትን ከዛሬ የሚያስተሳስር ለኅብረ ብሔራዊነት የሚሠራ ነው ብለዋል። ለችግር ሳይበገር ከችግር በላይ ኾኖ የሠራ ፓርቲ መኾኑንም ገልጸዋል። ሰላምን በማጽናት፤ ልማትን በማስቀጠል እየሠራ እንደሚገኝም ገልጸዋል።

ብልጽግናን በመምረጥ የሀገርን ዕድገት ማስቀጠል እንደሚገባቸውም አንስተዋል።

ዘጋቢ:- ያየህ ፈንቴ

የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ

https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !

Previous article“የሀገር ዘላቂ ልማት እና ሰላም የአብን ቀዳሚ አጀንዳዎች ናቸው” በለጠ ሞላ (ዶ.ር)
Next articleጽንፈኛውን የማጽዳት ግዳጃችን አመርቂ ውጤት እያስመዘገበ ነው።