“የሀገር ዘላቂ ልማት እና ሰላም የአብን ቀዳሚ አጀንዳዎች ናቸው” በለጠ ሞላ (ዶ.ር)

5

 

ባሕር ዳር: ግንቦት 01/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ቅድመ ዝግጅት፣ በሀገራዊ እና ቀጣናዊ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ የውይይት መድረክ በአዲስ አበባ እያካሄደ ነው።

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ሊቀመንበር በለጠ ሞላ (ዶ.ር) ፓርቲው ለሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ዴሞክራሲያዊነት የሚጠበቅበትን ገንቢ ሚና እንደሚወጣ ገልጸዋል።

የሀገር ዘላቂ ልማት እና ሰላም የፓርቲው ቀዳሚ አጀንዳዎች ናቸው ብለዋል።

የአንድ ሀገር ጠቅላላ ምርጫ ስኬታማነትም ዘላቂ ልማትና ሰላምን በማስቀጠል የሕዝብን ተጠቃሚነት የሚያጸና መሠረት መኾኑን ገልጸዋል።

በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ የተለያዩ የመገናኛ ብዙኅን አማራጮችን በመጠቀም የፖሊሲ አማራጫቸውን እያስተዋወቁ እንደሚገኙም ተናግረዋል።

በምርጫ ዝግጅት ምዕራፍ የፖሊሲ አማራጮች ታትመው ዛሬ ለመድረክ ተሳታፊዎች አንደሚታደሉ አስታውቀዋል።

በመድረኩ በምርጫ እና ድህረ ምርጫ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ ሀሳቦች እና የፓርቲው ሚና ምን መኾን እንዳለበት ውይይት ይደረጋል ብለዋል።

ፓርቲው ለሰላም፣ ለልማት እና ቀጣይነት ላለው ሀገራዊ ዕድገት የሚጠበቅበትን ገንቢ ሚና እንደሚወጣም ተናግረዋል።

ኢዜአ እንደዘገበው ለሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ፓርቲያቸው ለምርጫ ሂደት ዴሞክራሲያዊነት የሚጠበቅበትን ሚና እንደሚወጣም አንስተዋል።

የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ

https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !

Previous articleደረጃውን የጠበቀ የዓሣ ማስገሪያ በመጠቀም የዓሣ ሀብት ልማትን ለማሳደግ እየተሠራ ነው።