
ባሕር ዳር፡ ግንቦት 01/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ኢራን ከአሜሪካ የቀረበላትን የሰላም ጥያቄ እየመረመረች መኾኑ ተገልጿል። ምላሽ ለመስጠትም እስካሁን ምንም ዓይነት የጊዜ ገደብ እንዳላስቀመጠች ማስታወቋን አልጀዚራ ዘግቧል።
ቴህራን ሂደቱ በደረጃ እንዲከናወን ፍላጎት እንዳላትም አስታውቃለች። ስለ ኒውክሌር መርሐ ግብሯ ድርድር ከመጀመሩ በፊት ቀጣናዊ ግጭቶች እንዲቆሙ እና የተጣሉባት የኢኮኖሚ ማዕቀቦች እንዲነሱ ቅድመ ሁኔታም አቅርባለች።
በሆርሙዝ የባሕር ሰርጥ የጸጥታ ሁኔታ እና በዩራኒየም የማበልጸግ ሂደት ላይ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው አለመግባባት አሁንም እንደቀጠለ ይገኛል።
ዘጋቢ፦ስማቸው አጥናፍ
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ
https://linktr.ee/Amharamediacorporations
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !
