
ባሕር ዳር፡ ግንቦት 01/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት የተመራጩ ፕሬዝዳንት ኢስማኤል ኦማር ጊሌን የበዓለ ሲመት ሥነ ሥርዓት ለመታደም ዛሬ ጅቡቲ ተገኝቻለሁ ብለዋል።
ፕሬዝዳንት ኢስማኤል ለሃገራቸው የሚሰጡት አገልግሎት ሁለንተናዊ እድገትን እንዲያስቀጥል ልባዊ ደስታዬንና መልካም ምኞቴን ልገልጽ እወዳለሁ ነው ያሉት።
በኢትዮጵያ እና በጅቡቲ መካከል ያለው የቆየ ወዳጅነት እና ስትራቴጂካዊ አጋርነት ለሕዝቦቻችን የጋራ ብልጽግና፣ ለቀጣናችን ሰላምና መረጋጋት መጠናከር መሠረት እንዲኾን እመኛለሁ ብለዋል በመልዕክታቸው።
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ
https://linktr.ee/Amharamediacorporations
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !
