
አዲስ አበባ: ሚያዝያ 30/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የሰላም አማራጭን የተቀበሉ በአማራ ክልል ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የቀድሞ ታጣቂዎች በአዲስ አበባ ከተማ የልማት ሥራዎችን እየጎበኙ ነው።
ባለፋት ዓመታት በአማራ ክልል የተፈጠረው ግጭት የክልሉን ሕዝብ ለማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳት ዳርጎት ቆይቷል።
ግጭቱ ይፈታ ዘንድ በተደጋጋሚ የሰላም ጥሪዎች ሲደረጉ ቆይተዋል። የአማራ ክልል መንግሥት እና አፋሕድም የሰላም ስምምነት መፈራረማቸው የሚታወስ ነው።
ይህንን ተከትሎም የቀድሞ የታጣቂ መሪዎች እና አባላት የሰላም አማራጭን ተቀብለው እየገቡ ይገኛሉ።
ሰላምን ምርጫቸው ያደረጉ መሪዎች እና አባላት ከግጭት ወደ ልማት የሚያስገባ ሥልጠና ሲወስዱ ቆይተዋል። ዛሬ ደግሞ በአዲስ አበባ ከተማ የተሠሩ የልማት ሥራዎችን እየጎበኙ ይገኛሉ።
ዘጋቢ፦ ኢብራሒም መሐመድ
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ
https://linktr.ee/Amharamediacorporations
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !
