ብልጽግና ፓርቲ የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየሠራ ነው።

4

 

ከሚሴ፡ ሚያዚያ 30/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ብልጽግና ፓርቲ በኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር ከሚሴ ከተማ የምርጫ ቅስቀሳ አካሂዷል።

የከሚሴ ከተማ አሥተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ መሀመድ አሊ በከተማ አሥተዳደሩ የኅብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ፓርቲው ኢኒሼቲቮችን በመለየት ተግባራዊ ኦያደረገ ነው ብለዋል።

በከተማ ግብርና ዘርፍ ሰፋፊ ክላስተሮችን በመፍጠር የአርሶ አደሮችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየሠራ መኾኑንም አንስተዋል።

የከሚሴ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ ሸሪፍ ቃሲም ከተማ አሥተዳደሩ በበጀት ዓመቱ የሕዝቡን የልማት ጥያቄዎች ለመመለስ ከ500 ሚሊዮን ብር በላይ በኾነ ወጭ ፕሮጀክቶችን እየገነባ መኾኑን ገልጸዋል።

ብልጽግና ፓርቲ ለበርካታ አቅመ ደካሞች ቤት በመሥራት ማስረከቡን አስረድተዋል።

ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊ እና ዴሞክራሲያዊ ኾኖ እንዲጠናቀቅ ከተማ አሥተዳደሩ እየሠራ መኾኑንም አብራርተዋል።

የብልጽግና ፓርቲ አባላት እና ደጋፊዎችም በምርጫው ድምጻቸውን ለመስጠት ካርዳቸውን በማውጣት በመጠባበቅ ላይ መኾናቸውን ጠቅሰዋል።

ዘጋቢ:- ይማም ኢብራሒም

#የ7ኛው_ጠቅላላ #ምርጫ_አማራ #ክልል #Ethiopia 🇪🇹

የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ

https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን !

Previous articleመሪውን በምርጫ የሚሾም እና የሚሽር ማኅበረሰብ ለመገንባት ምሁራን የድርሻቸውን ሊወጡ ይገባል።
Next articleየሰላም ጥሪን የተቀበሉ የቀድሞ ታጣቂዎች በአዲስ አበባ ከተማ የልማት ሥራዎችን እየጎበኙ ነው።